1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማሕበራቂ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

ቅዳሜ፣ ሰኔ 10 2015

"አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ "ይላሉ አበው በንግግራቸው። በመሪዎቹ እብሪት ወንድማማች ህዝቦች ደም ተቃቡ፤አሁን እነሱ እርስ በርሳቸው ይሸላለማሉ ይሞጋገሳሉ። ይሄ ለህዝቡ ያላቸዉን ንቀት የገለፁበት ነው። በአጠቃላይ ስምምነቱ ህዝብን መሰረት ያላደረገ የይስሙላ እርቅ ነው።“

https://p.dw.com/p/4Si6M
Facebook, Twitter, Instagram, TikTok
ምስል Hideki Yoshihara/AFLO/IMAGO

የማሕበራቂ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች መልኩን እና የግጭት መንስኤው እየቀያየረ በሚያጋጥም ግጭት በርካታ ሰላማዊ ዜጎች፣ ታጣቂዎችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት መሞት መቁሰላቸውን ሰሙኑ የማሕበራዊ መገናኛ ብዙሃን በስፋት ሲንu።r።ሸሩ ከቆዩ ፍጻሜዎች ናቸው።
በሌላ ወገን ደግሞ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ መስተተዳደር ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና የአማራ ክልል ርእሰ መስተደዳር ዶክተር ይልቃል ከፍአለ በባሕርዳር ከተማ ተገናኝተው ተወያይተዋል። በውይይታቸውም ማንኛውም ጥያቄ ቢኖር ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት፣ የተዘጉ መንገዶች ተከፍተው የሕዝብ ለሕዝብ ግኑኝነት እንዲጀመር፤ የንግድ እንቅስቃሴም እንዲጀመር፤ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ በሚሉ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት እንደደረሱ ከሕዝብ ተወካዮች ፊት ቀርበው መናገራቸውን ተዘግቧል።
በነዚህ ጉዳዮች ላይ ከተንሸራሸሩት ሐሳቦች ከስድብ የነጹትንና የግለሰብ ስብዕናን የማይነኩትን መርጠን እንደሚከተለው እናቀርባለን።

 ጌታቸው ማሞ የተባሉ “ከውጭ የመጣ ጠላት የለም፣ እርስ በእርሳችን ነው እየተገዳደልን ያለነው፣ መንግስት ሕግ ማስከበር የሚለው የአማራን ሀይል ለመበተን ያለመ መሆኑን የተረዳው የአማራ ሕዝብ እምቢተኝነቱ ስህተት ሊሆን አይገባም፣ ብሶት የወለደው ራሱን የመከላከል መብት ነው፣“
 በማለት ሐሳባቸውን አስፍረዋል።
አብዱሰላም ደግሞ ሀሳባቸውን በጥያቄ ማስፈርን የመረጡ ይመስላል። “ኢትዮጵያ ውስጥ የሠው ህይወት ሣይጠፋ ወይም ሠው ሣይገደል የሚቀርበት ቀን መቸ ነው?“

"ኦሮሚያ ላይ ያለዉ ህዝብ ገለዉ አፈናቅለዉ አልበቃቸዉ ብሎ በተቀመጥንበት መጥተዉ ያርዱናል።መከላከያ ማለት ዳር ድበር የሚያስከብር እጂ መሃል ሀገር ምን ይሰራል?“
በማለት ሐሳባቸውን ያሰፈሩት ደግሞ አኔክስ ላቭ ተረፈ በሚል መጠሪያ የሚታወቁ አስተያየት ሰጪ ናቸው። ተመሳሳይ ሐሳብ ያጋሩት ደግሞ እዮብ በላይ ናቸው።
“ሱደን 80 ኪ.ሜ ስትወረን ምንም ሳይል መሀል ገብቶ የፖሊስ ስራ ካልሰራሁ ብሎ ያሸብራል፡፡“
በማለት ይወቅሳሉ።  ይህን ሃሳብ በመቃወም ሱልጣን መሐመድ ያሰፈሩት ሃሳብ
„“የአገር መከላከያ ሰራዊትን የሚያክል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ኩራት በማንም የመንደር ታጣቂ  ደሙ ሲፈስ ይኖራል። የአገር አለኝታና መከታ የሆነው መከለካያችን እንዲሁ እንደ ቀልድ?ያሳዝናል  ያስተዛዝባልም ጭምር!“ ይላል።
 GTZኢትዮጵያ የሚል መጠሪያ የሚጠቀም ወይም የምትጠቀም ደግሞ ተከታዩን አስፍሯል
በዘውግ አገዛዝ ሠላም የለም
ብልፅግና በዘውግ ላይ የተመሰረተ መሆኑን የምታዬው በተግባር እንዲህ ነው።
ብልጽግና በጦርነት ይጨርስህና ያስጨርስና ጨፍጫፊውን የሠላም አምባሳደር ብሎ የሚሸልም ሸረኛ ፓርቲ ነው!
ቶማስ ሳንካራ የተባሉት ያስቀመጡት አጭር አስተያየት ደግሞ `` በሰበብ አስባቡ አማራን የመግደል አባዜ የተጠናወተው ስርዓት``

በትግራይ እና በአማራ ክልሎች  ርዕሳነ መስተዳድሮች ውይይት ላይ ተንተርሰው ወደተሰጡ አስተያየቶች ስናልፍ
“የአሁኑም ቢሆን ከይስሙላ የዘለለ የሰላም ወይይት አይሆንም ምክነያቱ ደግሞ የሁለቱም ክልል ሚዲያዎች እያሠራጩ ያሉት የወሰን ይገባኛል ጥያቄ ውይይትን ያስቀደመ አይመስልም“
ሚክኤል ቦግአለ።
በአለም ታሪክ ጦርነቶች የሚካሄዱት ለአንድ አላማ ነው።
ይህ ግን እየው በሚሊዮን የሚቆጠሩ የደሀ ልጆች እንደ ቅጠል ረግፈው ቢሊዮንስ ዶላሮች አመድ አድርገው አሁን ጦርነት ከመጀመራችን በፊት ወደ ነበርንበት እንመለስ እያሉን ነው ። በእውኑ እንደዚህ የተምታታ መዳረሻ የሌለው ጦርነት በአለም ላይ ኖሮ ያቅ ይሆን?
ቼ ጉቤራ ያሰፈሩት ሃሳብ ነበር። ኪሩቤል ያዕቆብ ደግሞ
“እርቅና ሰላም ለማድረግ መቼም ቢሆን አይዘገይም ።
በሰሜኑ ጦርነቱ በሚልዬን የሚቆጠር ሰው ማለቁ በጣም ልብን የሚሰብር ቢሆንም በቀጣይ ሌላ ጦርነት ተከፋቶ ብዙ ሚሊዬን ሰው እንዳያልቅ ለሰላም መስራቱ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው።“
ፋንታሁን አወቀ ደግሞ መንግስት ከአለፈው ስህተቱ መማር አለበት በማለት ሐሳባቸውን ይጀምራሉ

“አሁንም ቢሆን መንግስት ከባለፈው ስህተት መማር አለበት። በተለይ የምዕራብ ትግራይ እና የደቡብትግራይ በአስቸኳይ መፍትሔ መሰጠት አለበት። አለበለዚያ ከድጡ ወደ ማጡ   ይሆናል“ ሲሉ ሃሳባቸውን አጠቃለዋል።ሰላም Dw እንዴት ናችሁ ሰላም ከእንጀራ ይጣፍጣል። ሞቼ እገኛለሁ ማለት ጎዳን በማለት ሃሳባቸውን በአጭሩ ያስቀመጡት ደግሞ መሐመድ ሰይድ የተባሉ የፌስ ቡክ ተጠቃሚ ናቸው።

Meta Logo
ምስል KIRILL KUDRYAVTSEV/AFP

"አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ "ይላሉ አበው በንግግራቸው። በመሪዎቹ እብሪት ወንድማማች ህዝቦች ደም ተቃቡ፤አሁን እነሱ እርስ በርሳቸው ይሸላለማሉ ይሞጋገሳሉ። ይሄ ለህዝቡ ያላቸዉን ንቀት የገለፁበት ነው። በአጠቃላይ ስምምነቱ ህዝብን መሰረት ያላደረገ የይስሙላ እርቅ ነው።“
ቢረሳው ቀለሙ በበኩላቸው  የሚሻለው ሠላም ስለሆነ አጥፊ ይቅርታ ከጠየቀ ይቅር ማለት ከህዝብ ይጠበቃልና ይቅር ተባብለን አብረን ሰማዕታትን እየዘከርን ብንኖር ሁላችንም እንጠቀማለን እላለሁኝ።“

ሰሞኑን በሴት ልጅ ጠለፋ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኗ በሰነበተችው ሀዋሳ ከተማ በድጋሚ በአንዲት የ14 ዓመት አዳጊ ላይ ተመሳሳይ ድርጊት መፈፀሙ እየተነገረ ይገኛል ፡፡ ጠለፋው ሜላት መሀመድ በተባለች አዳጊ ላይ ተፈጸመ የተባለው በተለምዶ ሞኖፖል ተብሎ በሚጠራው ሠፈር ውስጥ ነው ፡፡ 
ግለሰቦቹ ጠለፋውን የፈጸሙት ዳማስ በመባል በሚታወቁ ሁለት አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች መሆኑን በአካባቢው ነበርን ያሉ ሰዎች እንደነገሯቸው የአዳጊዋ ቤተሰቦች ገልጸዋል ፡፡ የመንደሩ ሰዎች በተሽከርካሪዎቹ ላይ ድንጋይ በመወርወር ሜላትን ለማስጣል ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው ነው የሜላት አክስትና አሳዳጊ ወ/ሮ ምኞት ተሾመ ለዶቼ ቬለ (DW) የተናገሩት ፡፡
የጠለፋ ድርጊቱ የተፈጸመው አዳጊ ሜላት ከትምህርት ቤት መልስ ወደ ቤቷ ለመግባት ጥቂት ርምጃዎች ሲቀራት መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ ምኞት «ሜላት ወላጅ እናቷ በሕይወት ከተለየች ወዲህ ያሳደግናት እኛ ነን ፡፡ ዘንድሮ የ8ኛ ክፍል ብሄሔዊ መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ በዝግጅት ላይ እያለች ነው ድርጊቱ የተፈጸመባት ፡፡ በአሁኑ ወቅት ጉዳዩን ለታቦር ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ አመልክተናል ፡፡ የጣቢያው ፖሊስ ባልደረቦችም ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ» ብለዋል ፡፡
በአዳጊ ሜላት መሀመድ ጠለፋ ዙሪያ ዶቼ ቬለ የከተማውን ፓሊስ መምሪያ ኃላፊዎች በአካልም ሆነ በሥልክ ለማነጋገር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም ፡፡ መምሪያውም ቢሆን እስከአሁን በጉዳዩ ላይ ያለው ነገር የለም ፡፡
በሀዋሳ ከተማ ከሁለት ሳምንታት በፊት በአንድ የባንክ ሠራተኛ ወጣት ላይ ተመሳሳይ የጠለፋ ድርጊት በሀዋሳ ከተማ ከንቲባ የግል ጠባቂ መፈጸሙ ይታወቃል ፡፡ የጠለፋ ድርጊቱን ፈጽሟል በሚል ሲፈለግ የነበረው ተጠርጣሪም ከዘጠኝ ቀናት ፍለጋ በኋላ በሕግ ቁጥጥር ሥራ ውሎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ ፖሊስ ማስታወቁ አይዘነጋም ፡፡ 

የሚል ዘገባ በDW እና በሌሎች ዓለምአቀፍና የሃገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ከተዘገበ ቦኋላ በማህበራዊ መገነኛ ዘደዎች በርካታ ሃሳቦች ተንሸራሽሯል። ቁጥራቸው የማይናቅ አስተያየቶች ችግሩን አቅልሎ የማየትና እንደውም እኛም በመዘገባችን የሚወቅሱ ዘመኑን ያልዋጁ አስተያየቶችም ሰፍረዋል። እነዚህን ትተን የተወሰኑትን ሃሳቦች እናቀርባለን።

“ፖሊስ መጥለፍ ሲጀምር ምን ይደረግ“ የሚል አስተያየት የሰጡት ገላጋይ ታደሰ ናቸው። ደሰድ ማንድ በሚል መጠሪያ የሚታወቁት አስተያየት ሰጪም “የቆየ የብዙዎችን ልጃገረዶች ህይወት ያጨለመና ሐይ ሊባል የሚገባው ልማድ ነውና  የክልሉ መንግስት ና ህዝቡ እንዲያስቆሙት ክልል አቀፍ ዘመቻ ያስፈልጋል።“ ብለዋል።
ሸምስ መሃመድ „ሆን ተብሎ የሚሰራ ጉዳይ ይመሰላል።“ የሚል ዘጭር አስተያየት አስቀምጧል።
ሰው አይሰለጥንም እንዴ በ21ኛው ክፍለ ዘመን እንዲህ አይነት ድርጊት እንዴት ይፈጸማል በማለት አስተያየታቸውን የሰጡት ደግሞታንጉት ዳኘው ናቸው።

ባሳለፍነው ሰኔ 2 ቀን፣ 2015 በደመቀ ሁኔታ የተከናወነው «9ኛው የጉማ አዋርድ» የሽልማት ስነስርዓት መርኃ ግብር ማምሻው ላይ በተከሰተው አስደንጋጭ የእስር ሁኔታ ነበር የተጠናቀቀው ። ብዙዎች እስሩን የመናገር እና ሐሳብን በነፃ የመግለጽ መብትን የሚደፈልቅ ተግባር በማለት ኮንነውታል፤ በስፋትም ተወያይተውበታል ። 
እስሩ የተፈጸመው በሽልማት አሰጣጡ ወቅት የታደመችው የቴሊቪዥን መርኃ ግብር አዘጋጅ እና የቲክቶክ ተጠቃሚ ፍላጎት አብርሀም በገጸ ቅብ ለየት ባለ አቀራረብ ከታየየች በኋላ ነው ። በማኅበራዊ መገናኛ አውታር «ልጅ ማኛ» በሚል መጠሪያ የምትታወቀው ፍላጎት ግንባሯ ላይ በጥይት የተበሳ ምልክት አድርጋ፤ ከንፈሮቿንም እንዳትናገር በሽቦ ተሰፍቶ የተጠረቀመ አስመስላ እና በሙሽራ ልብሷ ስር የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በደብዛዛው እንዲታይ አድርጋ ነበር መድረኩ ላይ የታየችው ። ጋዜጠኞች ሲጠይቋትም ምንም አልተናገረችም ። 
በስተመጨረሻ የሽልማት ስነስርዓቱ አዘጋጅ እና የፊልም ባለሞያ ዮናስ ብርሃነ መዋ እንዲሁም የቴሌቪዥን ታዋቂ አቅራቢዋ ፍላጎት ለእስር ተዳርገዋል ። ድርጊቱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር  ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፦ «ጥበባዊ ገለጻ ሐሳብን የመግለጽ መብት ወሳኝ አካል ነው። በአስቸኳይ ፍቷቸው» ሲሉ በትዊተር እና የፌስቡክ የማኅበራዊ የመገናኛ አውታር ይፋዊ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል ። የፊልም ባለሞያው ዮናስ ብርሃነ መዋ ከሁለት ቀናት እስር በኋላ መፈታቱ ተዘግቧል ። ይህ ዘገባ በDW እና በሌሎች መገናኛ ብዙሃን ሰፌ ሽፋን ያገኘ ነበረ። ይህን ተንተርሶ የሃገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት የደረሰበትን ዝቅተኛ ደረጃ እንደሚያመላክት ብዙዎች በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ጽፈዋል። የተወሰኑትን እናቀርባለን።
``እዚህ ሀገር ነጻነት የሰዉ ስም ከሆነ ቆየ እኮ`` የሚል አጭር አስተያየት የጻፉት ልጅ ሚኪ ናቸው። መይሳው በላይ ደግሞ ``ኢትዮጵያ ውስጥ ሐሳብን በነፃነት መግለፅ ወንጀል ነው። ማረሚያ ቤቱን የሞሉት ታሳሪዎች ሀሳባቸውን በነፃነት በሚገልፁ የመብት ተማጋቾች ናቸው።`` ብሏል። ሚኪኤል ቦጋለም ``ስንቱ ለሚዲያ ቅርብ ያልሆነና መንግስት በሚፈፅማቸው የመብት ጥሰቶች በተለያየ መንገድ ድምፅ የሆኑ ወገኖች ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በየእስር ቤቱ እየማቀቁ የገኛሉ። በአሁኑ ሰአት ከህወሀት በበለጠ መልኩ ሀሳብን በነፃነትን መግለፅ እንደወንጀል የሚታይ ሆኗል።`` በማለት ጽፏል።
``በመጀመሪያ እኔ ለእናንተ ለ DW Amharic ቀላል ጥያቄ አለኝ፥
እንኳንስ በዚህ መንገድ የተናገረ እና ተቃውሞውን በዚህ መንገድ የገለፀ ሰው እንዲሁ ሀሳቡን ለራሱ በልቡ ይዞ የራሱን ሕይወት ብቻ እየኖረ ምንም ነገር ሳያደርግ የታሰረ ብዙ ዜጋ እንዳለ አታውቁምን? ይቅርታ ግን የሀሳብ ነፃነት... ምናምን ጉዳይ በኢትዮጵያ ለጊዜው ይቆየን እና በእንደዚህ ዓይነት ስራችሁ ለእኔ የምትገርሙኝ እናንተው ናችሁ። `` ያሉን ተስፋለም መሃሪ ናቸው። በበኩላችን ይህን መዘገባችን ምኑን እንደገመዎት ገርሞን አልፈነዋል።

Symbolbild Facebook & Meta | Pfeil nach unten
ምስል Jakub Porzycki/NurPhoto/picture alliance
Twitter unter Elon Musk: Ein halbes Jahr im Krisenmodus
ምስል CHRIS DELMAS/AFP via Getty Images

``ሀሳብን በነፃ  የመግለጽ መብት ኢትዮጵያ ውስጥ እንኳን ሚድያ ላይ ከዚህም ውጪ ከተከለከለ ቆየ። አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ህግ ሰሪው ህግ የሚጥስበት ሰኣት ላይ ነው። የራሷን ህግ ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ የፈረመችባቸውንም ከተጣሱ ቆዩ ስለዚህ አይግረመን፤ ለመድነው እኮ! ሲናገሩ መታሰርን የአሁኑ ለየት የሚያደርገው በዝምታ እና በጥበብ በመናገሯ መሆኑ ነው።
ዝምታም ያስፈራል !``
ያሉት ይትባረክ ጌታቸው የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ናቸው።
``የመናገርና ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ የዜጎች ሁሉ መብት መሆን አለበት እንጂ በታሪክ አጋጣሚ "ስታዲዬምና ስቱዲዮ" ለያዘ ቡድን ብቻ የተሰጠ መሆን የለበትም። ሌላው ሲናገር "ጥላቻ" ያ ቡድን ሲናገረው "የመናገር መብት" የሚሆነው ነገር ይገርመኛል። አንዱ ሲታሰር መጮህ ሌላው ሲታሰር ዝም የሚሉ  ሚዲያዎችም የቡድን ድምፆች እንጂ የህዝብ እንዳልሆኑ ማሳያ ነው። አለምአቀፍ ሚዲያ እንኳን መንደርተኛ ሲሆን መንግስትን ለመውቀስ ምን ሞራል ይኖረዋል? ስለዚህ አንዲት ክስተት ላይ አተኩሮ ማስጮሁ ቀርቶ መሠረቱን መገንባት ይመረጣል።`` ያሉት ደግሞ ወርቁ በዳዳ ናቸው።
``አንድ ግለሰብ ጥሪ ሳይደረግለት በፕሮግራሙ ላይ ተሸላሚ ሳይሆን ዝም ብሎ ገብቶ የፈለገውን ማድረግ መብት የለውም ።መድረኩ የፖለቲካ መድረክ አልነበረም። ልጅቷ የቀድሞ የኢትዮጵያ ባንድራ ለምን ተጠቀመች? በህግ የታገደ የተቀየረ ነው። ይኼ ራሱ ስህተት ነው`` ያሉት ደግሞ ጉታ ቶላ ናቸው።
ውድ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት ታዳሚዎች ለዛሬ ያልነው በዚሁ ፈጽመናል።

ዮሀንስ ገብረእግዚአብሄር 

ታምራት ዲንሳ