Eshete Bekeleረቡዕ፣ ታኅሣሥ 23 2017ኢትዮጵያ በጠና የታመሙ ሰዎች “የአንጎል ሞት ሲረጋገጥ” በመሣሪያ ላይ ብቻ የተመሠረተ ሰው ሠራሽ የአተነፋፈስ ዕገዛ ማቋረጥን የሚፈቅድ ሕግ አጸደቀች። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ሁለት የአምቡላንስ ሾፌሮች በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች በተፈጸመባቸው ጥቃቶች ቆሰሉ። የዋጋ ግሽበት “ከፍተኛ እና በመካከለኛ ጊዜ ሊደረስበት ከታሰበው የባለ አንድ አኃዝ ግብ በላይ መሆኑን” የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ገለጸ። የአፍሪካ ኅብረት የድጋፍ እና ማረጋጋት የሶማሊያ ተልዕኮ (AUSSOM) በይፋ ሥራ ጀመረ። የአይቮሪ ኮስት ፕሬዝደንት አላሳን ዋታራ የፈረንሳይ ወታደሮች በዓመቱ መጨረሻ ከሀገራቸው ለቀው እንደሚወጡ አስታወቁ።