Eshete Bekeleሰኞ፣ ጥር 5 2017የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት “የሲቪክ ምኅዳሩን የሚያጠቡ እርምጃዎች ከመዉሰድ በመቆጠብ በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት በተደነገገው መሠረት ለመደራጀት መብት ያለውን ቁርጠኝነት እንዲያረጋግጥ” 50 የመብቶች ተሟጋች ድርጅቶች ጠየቁ። በጦርነት ከቀያቸው ተፈናቅለው በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የተጠለሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሔዱ። በናይጄሪያ ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ ከሚጠራው ታጣቂ ቡድን የወገኑ ኃይሎች በፈጸሙት ጥቃት ቢያንስ 40 ገበሬዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ተናገሩ። ቃጣር የጋዛን ጦርነት ለማብቃት የተዘጋጀ ሥምምነት የመጨረሻ ረቂቅ ለእስራኤል እና ለሐማስ ተደራዳሪዎች አቀረበች።