ሥጋት ያጠላበት የአዲስ አበባ - ሀዋሳ መንገድ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 22 2015ማስታወቂያ
የ 278 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍነው የአዲስ አበባ ሀዋሳ መስመር እስከቅርብ ጊዜ ድረስ አንጻራዊ ሰላም የሰፈነበት ፤ ለአሽከርካሪዎችና ተጓዥችም ምቹ ተደርጎ ይወሰድ ነበር ፡፡ ካለፉት ሦስት ወራት ወዲህ ግን መንገደኞች በፀሎት ፤ አሽከርካሪዎች ደግሞ በሥጋት የሚጓዙበት እየሆነ መምጣቱን የህዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪዎች ይናገራሉ፡፡ አሽከርካሪዎቹ እንደሚሉት በመስመሩ ድንገት ብቅ የሚሉ ታጣቂዎች ይዘርፋሉ ፣ ይገድላሉ ፣ ተሸከርካሪዎችን ያቃጥላሉ ፡፡
በአብዛኛው ጥቃቶቹ የሚፈጸሙት በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ባቱ እና መቂ በተባሉት ወረዳዎች ውስጥ ነው ይላሉ አሽከርካሪዎቹ ፡፡ በዚህም የተነሳ ሥራቸውን በስጋት ውስጥ ሆነው ለማከናወን መገደዳቸውን ነው ሥማቸው በሚስጥር እንዲቆይላቸው የጠየቁ አሽከርካሪዎች ለዶቼ ቬለ የገለጹት፡፡ አሽከርካሪዎቹ መንግሥት ያጋጠማቸውን የደህንነት ሥጋት በመቅረፍ የመሥመሩን ሰላም እንዲያስጠብቅም ጠይቀዋል፡፡
ዶቼ ቬለ በጉዳዩ ላይ የባቱ እና መቂ ወረዳዎችንም ሆነ የኦሮሚያ ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊዎችን ምላሽ ለማካተት ያደረገው ጥረት ሃላፊዎቹን ማግኘት ባለመቻሉ ለጊዜው አልተሳካም፡፡
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ