በሐጫሉ ግድያ የተጠረጠሩና የእነ አቶ ጀዋር የፍርድ ሒደት
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 6 2013ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የተጠረጠሩ ተከሳሾችን የመከላከያ ምስክሮች ቃል ዛሬ አድምጧል። አንደኛ ተከሳሽ ጥላሁን ያሚ እና ሁለተኛ ተከሳሽ ከበደ ገመቹ እያንዳዳቸዉ ሁለት ሁለት መከላከያ ምስክሮችን አቅርበዋል። ከዚሕ ቀደም በዋስ የተለቀቀዉ ሶስተኛዉ ተከሳሽ አብዲ ዓለማየሁ ዛሬ ያቀረባቸዉን ምስክሮቹን ለማድመጥ ፍርድ ቤቱ የችሎት ሰዓት ተጠናቅቋል በሚል ተለዋጭ ቀጠሮ ተስጥቷል። በሌላ በኩል በእነ አቶ ጀዋር መሐመድ ክስ የአቃቤ ሕግ ምስክሮች ቃል አሰማም ላይ የቃል ክርክር ለማድረግ ዛሬ ያስቻለዉ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የተከሳሾች ጠበቆች እስከ ዛሬ መጥሪያ አልደረሰንም በማለታቸዉ እና ተከሳሾች ከማረሚያ ቤት ሆነዉ ችሎቱን የሚከታተሉበት ፕላዝማ ባለመስራቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ስዩም ጌቱ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ