በእነ ጀዋር መሐመድ ላይ ምስክር ሊሰማ የነበረው ችሎት ለሌላ ጊዜ ተላለፈ
ሰኞ፣ ጥቅምት 22 2014ማስታወቂያ
በእነ አቶ ጃዋር መሃመድ የክስ መዝገብ ስር የተጠቀሱ 24 ተከሳሾች ላይ የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ቃል ለመስማት የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ለዛሬ ሰጥቶ የነበረው የችሎት ቀጠሮ ለሌላ ጊዜ ተላለፈ።
ችሎቱ ከተሰየመ የምስክር አሰማም ሂደቱ ያልተጀመረው በክስ ሂደቱ ላይ ጠቅላይ አቃቤ ህግ እና የተከሳሾች ጠበቆች በየፊናቸው ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ መጠየቃቸውን ተከትሎ መዝገቡ በመታገዱ ነው ተብሏል፡፡
ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለዛሬ ይዞ በነበረው ችሎት አቶ ጃዋር መሃመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሃምዛ አዳኔ እና አቶ ደጀነ ጣፋ በሌሉበት በግልጽ ችሎት የምስክሮችን ለመስማት ነበር ቀጠሮው ይዞ የነበረው፡፡
ይሁንና የተከሳሾች ጠበቆች አራቱ ተከሳሾች በሌሉበት የምስክር የመስማት ሂደቱ መጀመር የለበትም በሚል እና አቃቤ ህግ በበኩሉ ችሎቱ የምስክሮቹን ቃል ከመጋረጃ ጀርባ መቀበል አለበት በማለት ለጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤት ማለታቸውን ከጠበቆቹ አንዱ አቶ ቱሊ ባይሳ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡
ስዩም ጌቱ
ታምራት ዲንሳ
ማንተጋፍቶት ስለሺ