1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከታጣቂ ቡድኖች ጋር የሚደረጉ ድርድሮች እና ስምምነቶች ለምን አይነገሩም ?

እሑድ፣ ታኅሣሥ 27 2017

በተለያዩ ጊዜያት ከኦነግ ጋር የተደረጉ ድርድሮች ፤ ከኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ኦብነግ ጋር የተደረገ ድርድር እና ስምምነት ፤ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ፣ ከህወሓት ጋር እንዲሁም በቅርቡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አንድ ክንፍ ጋር የተደረጉ ድርድሮች እና ስምምነቶች ተጠቃሾች ናቸው ።

https://p.dw.com/p/4opj4
Äthiopien OLA Friegensabkommen in Oromia
ምስል Oromia communication

ድርድሮች እና ስምምነቶች ይፋ ያለመደረጋቸው አንድምታ

የኢትዮጵያ መንግስት ነፍጥ አንስተው ከሚዋጉት የተለያየዩ ታጣቂ ቡድኖች ጋር በተለያዩ ጊዜያት ድርድር  አልያም ንግግር አድርጎ ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። በ19 80ዎቹ እና በ2010 ከኦነግ ጋር የተደረጉ ድርድሮች ፤ ከኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ኦብነግ ጋር የተደረገ ድርድር እና ስምምነት  ፤ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ጋር በተመሳሳይ የተደረጉ ድርድሮች እና ከህወሓት ጋር የተደረጉ ድርድሮች  እንዲሁም በቅርቡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አንድ ክንፍ ጋር የደረጉ ድርድሮች እና ስምምነቶች ተጠቃሾች ናቸው ።

የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር ፈጸምኩ ያለው የሰላም ስምምነት ዳራ

ከእነዚህ ሁሉ የውጭ መንግስታት ጣልቃ ገብነት የታየበት  እና በመገናኛ ብዙኃን ጭምር ሰፊ ሽፋን የተሰጠበት እና የኢትዮጵያ መንግስት ከህወሓት ጋር ካደረገው ስምምነት ውጭ ሌሎች አብዛኞቹ ስምምነቶች በይፋ ለህዝብ ሳይገለጹ መቆየታቸው ይነገራል። መንግስት ከታጣቂ ቡድኖች ጋር የሚያደርጋቸው ስምምነቶች በይፋ አለመታወቃቸው ደግሞ በተለይ ስምምነቶች የሚጣሱበት ሁኔታ ሲፈጠር ተጠያቂውን ወገን ለመለየት አዳጋች እንዲሆን ከማድረግ  ባሻገር ፖለቲካዊ መፍትሄ የሚፈልጉ እና ለዘላቂ ሰላም መሰረት ሊሆኑ የሚችሉ ድርድሮችን ውጤት አልባ እንዲሆኑ እስከማድረስ ታይቷል።

Äthiopien OLA Friegensabkommen in Oromia
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በቅርቡ ከኦሮሞ ነጻነት ጦር ጋር የደረሰውን ስምምነት ተከትሎ ታጣቂዎች ከነሙሉ ትጥቃቸው እየተመለሱ እና ወደ ተሃድሶ ጣቢያዎች ሲገቡ ታይቷል።ምስል Oromia communication

የአማራ ክልል የሠላም ምክር ቤት የተደራደሩ ጥሪ

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በቅርቡ ከኦሮሞ ነጻነት ጦር ጋር የደረሰውን ስምምነት ተከትሎ ታጣቂዎች ከነሙሉ ትጥቃቸው እየተመለሱ እና ወደ ተሃድሶ ጣቢያዎች ሲገቡ ታይቷል። አዛዦቻቸው ደግሞ በተለያዩ መድረኮች ላይ የሀገሪቱን መከላከያ የደንብ ልብስ ለብሰው መግለጫ ሲሰጡ እና የልማት ስራዎችን ሲጎበኙ ይታያሉ ። ነገር ግን አሁንም ድረስ የክልሉ መንግስት ወይም የፌዴራሉ መንግስት ከታጣቂ ቡድኑ ጋር ስለተደረገ ድርድር እና ስለተደረሰበት ስምምነት በዝርዝር እና በይፋ ያሉት ነገር የለም።

የኦሮሚው የሰላም ድርድር

የታጣቂ ቡድኑ አባላት እና የአመራሩ መጻኢ ዕጣ ፈንታቸውን በተመለከተ እስካሁን በግልጽ የሚታወቅ ነገር የለም። የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ ታጣቂ ቡድኖች በድርድር ሰላም ለማውረድ የሚያደርጓቸው ድርድሮች እሰየው ቢያሰኙም ፤ ድርድሮቹ እና ስምምነታቸው በይፋ አለመታወቃቸው ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ አስቻይ እንዳልሆኑ ማሳሰቢያ ሲሰጥባቸው ይሰማል ።

´´ ከታጣቂ ቡድኖች ጋር የሚደረጉ ድርድሮች እና የተደረሱ ስምምነቶች ለምን አይነገሩም ?´´  የሳምንቱ የእንወያይ ዝግጅታችን ርዕስ ነው።

ታምራት ዲንሳ