1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቫይረሱ ሥርጭት አስደንጋጭ ነው

ታሪኩ ኃይሉ
ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 5 2017

"ዓለም አቀፍ ሲምፖዝየሙ በዋናነት ያተኮረው አንዱ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና ህክምና በተመለከተ፣ አሁን አሜሪካ ውስጥ ያሉ እመርታዎች ምንድን ናቸው የሚሉና የተመራመሩ ከፍተኛ ምሁራንን ያመጣነው"

https://p.dw.com/p/4o90Z
በደቡብ ካሮላይና ሜዲካል ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት የሲምፖዚየሙ አስተባባሪ ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ገብረ እግዚአብሄር
በደቡብ ካሮላይና ሜዲካል ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት የሲምፖዚየሙ አስተባባሪ ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ገብረ እግዚአብሄር ምስል privat

ሥርጭቱ አስደጋጭ ነው

 

በትግራይ ክልል የኤች አይቪ ኤድስ ስርጭትና መከላከል ስራዎችን በተመለከተ፣በደቡብ ካሮላይና ሜዲካል ዩንቨርስቲ፣ መቐለና አኽሱም ዩኒቨርስቲዎች እንዲሁም በትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ትብብር የተዘጋጀ ዓለም አቀፍ ሲምፖዚየም ተካሂዷል።

በትግራይ ክልል ከሁለት ዓመት በላይ በተካሄደው ጦርነት፣120 ሺህ ሴቶች ላይ ጾታዊ ጥቃት መፈጸሙና በውጊያው ምክንያት ለህሙማን መድኃኒት ማድረስ ሳይቻል መቆየቱ፣ለቫይረሱ ስርጭት መስፋፋት እንደ ምክንያት ከሚጠቀሱ ጉዳዮች መኻከል ይገኙባቸዋል። 

የሲምፖዚየሙ ፋይዳ

በየዓመቱ ኅዳር ወር ላይ የሚከበረውን የአለም ኤድስ ቀን አስታኮ የተካሄደው፣ ዓዓለም አቀፍ ሲምፖዚየም፣ስለበሽታው በትግራይ ክልል ግንዛቤ የመፍጠር ዓላማ አንግቦ መካሄዱን፣ በደቡብ ካሮላይና ሜዲካል ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት የሲምፖዚየሙ አስተባባሪ ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ገብረ እግዚአብሄር ለዶይቸ ቨለ ገልጸዋል።

"በጦርነቱ ሁለት ሦስት ዓመታት ስላሳለፈ እና ጦርነቱ ደግሞ የጤና ኢንስቲትዮሽን እንዲሁም የጤና ሠራተኞችን ያፈናቀለ፣ የጤና ተቋማትን ያፈረሰ በመሆኑ ምክንያት፣ በዚህም በተለይም የኤች አይቪ ኤድስ ታካሚዎች መድኃኒት የሚያገኙበት ዕድል ስላልነበረ፣ሊሰራበት የሚችል ጉዳይ እንደሆነ ተገንዝበን፣በዚሁ  ዘመቻ እንስራ ብለን ነው የተነሳነው።"

በትግራይ ክልል በአስጊ ሁኔታ እየተስፋፋ ያለውን የኤችአይቪ ስርጭት የመከላከል የመቆጣጠር አግባብ ያለው ስራ እንዲሰራ ጥሪ  ያቀረቡት ፕሮፌሰር ሙሉጌታ፣ሲምፖዚየሙ ከዚህ አኳያ ጠቃሚ ተሞክሮ የተገኘበት እንደሆነ አስረድተዋል።

"ዓለም አቀፍ ሲምፖዝየሙ በዋናነት ያተኮረው አንዱ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና ህክምና በተመለከተ፣ አሁን አሜሪካ ውስጥ ያሉ እመርታዎች ምንድን ናቸው የሚሉና የተመራመሩ ከፍተኛ ምሁራንን ያመጣነው"ብለዋል።

"በተለይም የኤች አይቪ ኤድስ ታካሚዎች መድኃኒት የሚያገኙበት ዕድል ስላልነበረ፣ሊሰራበት የሚችል ጉዳይ እንደሆነ ተገንዝበን፣በዚሁ  ዘመቻ እንስራ ብለን ነው የተነሳነው።"
"በተለይም የኤች አይቪ ኤድስ ታካሚዎች መድኃኒት የሚያገኙበት ዕድል ስላልነበረ፣ሊሰራበት የሚችል ጉዳይ እንደሆነ ተገንዝበን፣በዚሁ  ዘመቻ እንስራ ብለን ነው የተነሳነው።"ምስል Jens Kalaene/dpa/picture alliance

የቫይረሱ ሥርጭት አስደንጋጭ ነው

በትግራይ ክልል፣ በማኀበረሰቡ፣ ጦርነት ከቀዬአቸው ባፈናቀላቸው ወገኖችና በሴተኛ አዳሪዎች ያለውን የኤች አይ ቪ ስርጭት የተመለከተ ጥናት ተካሄዷል።
ጥናቱ፤በመቐለ፣ዓድዋ፣ዓዲግራትና ሽረ እንዳስላሰ መካሄዱን ለዶይቸ ቨለ የተናገሩት፣ በትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ተመራማሪ ወይዘሮ ክብርቲ መሐሪ፣ የተገኘው የኤች አይ ቪ ስርጭት ምጣኔ ብዙዎችን ያስደነገጠ መሆኑን ገልጸዋል።

"ብዙ መስራት እንዳለብን ነው"

"በጣም ነው ከፍ ያለውና በጣም አስደንጋጭ ነው እና  መንቃት አለብን ብለን ነው ያሰብነው።በማኀበረሰቡ ሦስት በመቶ መገኘት ማለት በጣም ብዙ ነውና ይሄ የሚያስፈራ ነው፤ ውጤቱን ብዙ መስራት እንዳለብን ነው።
በክልሉ፤በጦርነቱ ከቀዬአቸው በተፈናቀሉ ወገኖች እና በሴተኛ አዳሪዎች፣የኤች አይቪ ኤድስ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑን፣ወይዘሮ ክብርቲ ያስረዳሉ።
"አንድ ነጥብ ዘጠኝ በጦርነቱ በተፈናቀሉ ወገኖች ሌላው በሴተኛ አዳሪዎች በተወሰደው 1146 ናሙናዎች፣ስምንት ነጥብ ስድስት ነው ስርጭቱ የሚያሳየው፣ በጣም ብዙ ነው።"

ታሪኩ ሃይሉ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር