1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ፆታዊ ተፅኖዎች መቼ ይጀምራሉ?

ዓርብ፣ ጥቅምት 16 2016

ፆታዊ ተፅኖዎች መቼ ይጀምራሉ? በሴቶች እና ወንዶች መካከል ፆታን መሠረት ያደረጉ ልዩነቶችና ፆታዊ ተፅኖዎች ከቤተሰብ ይጀምራሉ “ ይላሉ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አመርቲ ጎበና እና በጸሎት ውብሽት ፡፡

https://p.dw.com/p/4Y2t9
የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሊሻን ዳኜ ፣ አመርቲ ጎበና እና በጸሎት ውብሸት
የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሊሻን ዳኜ ፣ አመርቲ ጎበና እና በጸሎት ውብሸትምስል S. Wegayehu/DW

ፆታዊ ተፅኖዎች መቼ ይጀምራሉ?

“ በአዳጊ ሴቶች እና ወንዶች መካከል በፆታ ምክንያት የሚስተዋሉ አመለካከቶች ከቤተሰብ ይጀምራሉ “ ይላሉ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አመርቲ ጎበና እና በጸሎት ውብሽት  ፡፡ የ12 ከፍል ጠማሪና የ 17 ዓመት ታዳጊ የሆኑት አመርቲ ጎበና እና በጸሎት በፆታ ምክንያት ለሚፈጠር የአመለካከት መዛባት ቤተሰብና ማህበረሰብ ትልቁን ድርሻ እነዳላቸው ይናገራሉ ፡፡  በልጅነት ዕድሚያቸው ቤተሰብ መጫወቻ ሲገዛላቸው  ለሴት የምግብ መሥሪያና የቡና ማፍሊያ ዕቃዎች  ለወንዶች ደግሞ ተሽከርካሪዎችንና መገጣጠሚያ የመሳሰሉ ዕቃዎችን በሥጦታ እንደሚያበረክቱላቸው የሚጠቅሱት አመርቲ እና በጸሎት “ ይህ የተዛባ አስተሳሰብ በአብዛኛው ቤተሰብ ውስጥ ሲንጸባረቅ ይስተዋላል “ ብለዋል ፡፡

ለልጆች መጫወቻ
ቤተሰብ ለልጆቻቸው መጫወቻ ሲገዛ  ለሴቶች የምግብ ማብሰያ ዕቃዎች  ለወንዶች ደግሞ ተሽከርካሪዎችንና መገጣጠሚያ የመሳሰሉ ዕቃዎችን እንደሆኑ የሚጠቅሱት አመርቲ እና በጸሎት በፆታ ምክንያት ያሉ አመለካከቶች ከቤተሰብ ይጀምራሉ “ ይላሉምስል Monika Skolimowska/dpa/picture alliance

በአዳጊ ሴቶች እና ወንዶች መካከል ፆታን መሠረት ያደረጉ ልዩነቶች በገጠር አካባቢዎች በግልፅ በከተሞች ደግሞ በሥውር የሚደረጉ መሆናቸውን የጠቀሰችው አመርቲ “ ለምሳሌ አስተሳሰቡ በተረቶችና በአባባሎች ይገለጻል ፡፡ በተለይ አንድ አዳጊ ሴት በፓይለትነት ወይንም በመካኒክ ሥራ መሠማራት እንደምትፈልግ የወደፊት ዓላማዋን ለመግለጽ ስትሞክር ትችያለሽ በሚል ከማበረታት ይልቅ አንቺ ሴት አይደልሽ አንዴት ይህን ታስቢያለሽ  የሚሉ ምላሾች  ይደመጣሉ “ ይላሉ  ፡፡

በዚህ የተዛባ አስተሳሰብ ዙሪያ አሁን ላይ በከተሞች አካባቢ የተወሰነ መሻሻል ቢኖርም ነገር ግን ብዙ መሠራት እንደሚኖርበት አዳጊዎቹ ይናገራሉ ፡፡ ለአብነትም በሚማሩበት ትምህርት ቤት አዳጊ ሴት ተማሪዎች በሁሉም ዘርፎች ላይ እንዲሳተፉ የሚያደርጉ ሥራዎች መኖራቸውን ታዳጊዎቹ ተናግረዋል ፡፡ በትምህርት ቤት በሚዘጋጁ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሴቶች ሌሎች ተማሪዎች በተሰበሰቡበት ሀሳባቸውን እንዲገልጹ የማበረታታት ጅምሮች መኖራቸውን ጠቅሰዋል ፡፡  ይህ ግን በቂ አይደለም የሚሉት ታዳጊዎቹ “ በተለይ የመገናኛ ብዙሃን በራሳቸው ጥረት ከትልቅ ቦታ ላይ የደረሱ ሴቶችን የህይወት ልምድ በማቅረብ ሌሎች ከዚህ እንዲማሩ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል “ብለዋል  ፡፡

ሊሻን ዳኜ / ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ልደት አበበ