የህወሓት መግለጫ እና አስተያየት
ሐሙስ፣ ሐምሌ 4 2011ማስታወቂያ
ህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ማክሰኞ ሐምሌ 2 2011 ካደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በኋላ ያወጣዉ መግለጫ በርካታ ሀገራዊ ጉዳዮች ዳሷል። በቅርቡ በከፍተኛ የሠራዊት አመራሮች ላይ የተፈጸመውን ግድያ በተመለከተም ጉዳዩን በሀገራዊ ገለልተኛ ወገን እንዲጣራ የጠየቀ ሲሆን ውጤቱም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይፋ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል። የሀገሪቱ ህልውና "ከመጥፎ ወደ ከፋ ደረጃ ተሸጋግሯል" ያለው ህወሀት የችግሮቹ ዋነኛ ምንጭም "የህዝብን መብትና ጥቅም ረግጠው ፍላጎታቸውን ሊፈፅሙ የሚፈልጉ የትምክህት ሀይሎች" ናቸው ብሏል። መግለጫው ከተለያዩ አካላት ድጋፍና ተቃውሞ እያስተናገደ ነው።
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ