የባሕርዳር ሕዝብ ጥያቄና ተቃዉሞ
ማክሰኞ፣ ጥር 19 2012ማስታወቂያ
ከደንቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ወደየቤተሰቦቻቸዉ ሲጓዙ እስካሁን ማንነታቸዉ ባልታወቀ ሰዎች የታገቱ ተማሪዎች እንዲለቀቁ የባሕርዳርና የአካባቢዉ ሕዝብ ባደባባይ ሰልፍ ጠየቀ። የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ተማሪዎቹ ተለቅቀዋል በማለት የሐሰት መረጃ ማሰራጨታቸዉን ሰልፈኛዉ አዉግዟል።የተለያዩ መፈክሮችን አንግቦ ባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዮም የተሰበሰበዉ ሰልፈኛ የፌደራሉ እና የዓማራ ክልል መንግስታት ባለስልጣናትን ተማሪዎቹን ለማስለቀቅ አልጣሩም በማለት ነቅፏቸዋልም።ዉግዘትና ነቀፋ የተፈራረቀባቸዉ የፌደራሉና የአማራ ክልል ባለስልጣናት ስለ ጉዳዩ እስካሁን በይፋ ያሉት ነገር የለም።ባለፈዉ ሕዳር ማብቂያ የተጋቱት ተማሪዎች እንዲለቀቁ ዘመቻ የጀመሩት ወገኖች እንደሚሉት አጠቃላይ ታጋቾቹ 17 ሲሆኑ፣ አብዛኞቹ ሴቶች ናቸዉ።
ዓለምነዉ መኮንን
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ