1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታሰሩ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ተጠየቀ

ሐሙስ፣ ኅዳር 3 2013

ከለውጡ ወዲህ መገናኛ ብዙሀን አንጻራዊ ነፃነት እንዳገኙ ያስታወሰው ማኅበሩ ግጭቶች ሲከሰቱ ግን በተወሰኑ ጋዜጠኞች ላይ ወከባ ጫናና እሥር መፈጸሙን ተቃውሟል።በአሁኑ ጊዜ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችም በአስቸኳይ እንዲለቀቁም ጠይቋል።

https://p.dw.com/p/3lD9h
Symbolbild - Interview
ምስል Fotolia/wellphoto

ጋዜጠኞች ከተለያዩ አካላት ወከባ እየደረሰባቸዉ ነዉ

 

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ማኅበር በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች መታሰር አሳሳቢ መሆኑን ገለፀ። የአዉሎ ሚዲያ አዘጋጅ ፤ የአዲስ ስታንዳር መጽሔት አዘጋጅ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋዜጠኞች እና የኦሮምያ ሚዲያ ኔት ዎርክ ጋዜጠኛ መታሰራቸዉን ተከትሎ ነዉ። የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ፤ የታሰሩት ጋዜጠኞች ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ጉዳያቸዉ እንዲታይ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ጥሪ ማስተላለፈፋቸዉ ይታወቃል። በኢትዮጵያ በሚከሰቱ የተለያዩ የፀጥታ ችግሮችን ተከትሎ ጋዜጠኞች ወከባ እስር እና የተለያዩ ተጽኖዎች እንደሚደርስባቸዉ ጋዜጠኞች ራሳቸዉ ይናገራሉ። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ማኅበር ምክትል ፕሬዚዳንት ኤርምያስ በጋሻዉ ለዶቼ ቬሌ እንደተናገሩት የመገናኛ ብዙኃን ስራ አንጻራዊ ነጻነት ታይቶበታል። ታስረዉ የነበሩ ተፈተዋል፤ ፈቃድ ተከልክለዉ የነበሩ በፈቃድ ይሰራሉ። ይሁንና ፤ አንጻራዊ ነጻነቱ እየደበዘዘ ነዉ። ጋዜጠኞች ከተለያዩ አካላት ወከባ እየደረሰባቸዉ ነዉ።     

ሰሎሞን ሙጬ


ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ