1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራይ ክልል በሁለቱ ዓመት ጦርነት የሞቱትን የቀድሞ ታጋዮች ቤተሰቦችን ማርዳት ተጀመረ

ዓርብ፣ ጥቅምት 2 2016

በጦርነቱ በትግራይ ወገን እየተፋለሙ የሞቱት ስንት መሆናቸው አሁንም በግልፅ ባይነገርም፥ በየአካባቢው እየተደረጉ ካሉ የመርዶ ስነ-ስነርዓቶች መታዘብ እንደሚቻለው፥ ጥቂት የማይባሉ ዕድሜያቸው በአስራዎቹ መጨረሻ፣ በሃያዎቹ መጀመርያ እና አጋማሽ የነበሩ ወጣቶች፣ ከጦርነቱ በፊት በተለያየ ሥራ አልያም ትምህርት የነበሩ፣ መሆናቸውን መረዳት ይቻላል።

https://p.dw.com/p/4XWDQ
ከጦርነቱ በፊት በተለያየ የስራ መስክ አልያም ትምህርት የነበሩ፣ ትግራይ ላይ የተከፈተው ጦርነት ተከትሎ ደግሞ ወደ ሰራዊት የተቀላቀሉ መሆናቸው ያመለክታል።
በትግራይ ወገን እየተፋለሙ የሞቱት ስንት መሆናቸው አሁንም በግልፅ ባይነገርም፥ በየአካባቢው እየተደረጉ ካሉ የመርዶ ስነ-ስነርዓቶች መታዘብ እንደሚቻለው፥ የህልፈታቸው ዜና እየተነገረ ካሉት የቀድሞ ታጋዮች መካከል ጥቂት የማይባሉ ዕድሜያቸው በአስራዎቹ መጨረሻ፣ በሃያዎቹ መጀመርያ እና አጋማሽ የነበሩ ወጣቶች ናቸው። ምስል Million Haileselasie/DW

የትግራይ ክልል በሁለቱ ዓመት ጦርነት የሞቱትን የቀድሞ ታጋዮች ቤተሰቦችን በይፋ ማርዳት ተጀመረ

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ከዛሬ ጀምሮ በጦርነቱ የሞቱትን የቀድሞ ታጋዮች ማንነት እያሳወቀ ነው። ከነገ ጀምሮ ደግሞ በመላው ትግራይ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሐዘን እንደሚታወጅም የክልሉ አስተዳደር አስታውቋል። በጦርነቱ ልጆቻቸውን እና ሌሎች ዘመዶቻቸውን ያጡ ቤተሰቦች ከመርዶ በኃላ ሐዘን ተቀምጠዋል። በትግራይ ክልል ከጦርነቱ ማብቃት አንድ ዓመት ገደማ በኃላ፥ በጦርነቱ ወቅት ከትግራይ ኃይሎች ጋር  ሆነው ሲዋጉ ያለፉት የቀድሞ ታጋዮች የማሰብ፣ መርዶ ለቤተሰቦች የመንገር እና የማፅናናት ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ስነስርዓቶች በሁሉም አካባቢ እየተከወነ ይገኛል። በመቐለ ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ሰሞኑን መታዘብ እንደሚቻለው የዘመዶቻቸው የህልፈት ዜና የተነገራቸው በርካታ ቤተሰቦች ሐዘን ተቀምጠዋል። በየአብያተ ክርስትያኑ እስከ ዛሬ ጠዋት ጠዋት ድረስ የቀጠለ የሞቱትን የማሰብ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ስነስርዓቶች እየተከወኑ ነው።

ለህልውናችን የተከፈለ በመሆኑ የሚያስቆጭ ባይሆንም በርካታ ልጆቻችን ከፍለናል" ብለዋል።እነዚህን የቀድሞ ታጋዮች ለማሰብም በርካታ ክልከላዎች ያሉት የሐዘን ቀን ከነገ ጀምሮ በትግራይ እንደሚታወጅ የክልሉ አስተዳደር አስታውቋል።
«ልንሰጠው ልንሰጠው ይገባል ሲባል ለእያንዳንዱ የተሰዋ ቤተሰብ ምስክር ወረቀት ፅፈናል።ስለዚህ ቁጥሩ በእጃችን አለ። ቁጥሩ አሳሳቢ አይደለም፣ ከባድ ዋጋ ከፍለናል። »ምስል Million Haileselasie/DW

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር በጦርነቱ ወቅት ያለፉ የቀድሞ ታጋዮች ለማሰብ ከነገ ቅዳሜ ጥቅምት 3 ቀን ጀምሮ እስከ ሰኞ የሚዘልቅ የሶስት ቀናት ብሔራዊ ሐዘን መታወጁ ያስታወቀ ሲሆን በእነዚህ ቀናት ሰማእታት ይታሰባሉ፣ ለቤተሰቦቻቸው መንግስት ይፋዊ መርዶ ይነግራል እንዲሁም እውቅና ይሰጣል ተብሏል። ትግራይ ክልል መርዶ መንገሩ ቀጥሏልበጦርነቱ በትግራይ ወገን እየተፋለሙ የሞቱት ስንት መሆናቸው አሁንም በግልፅ ባይነገርም፥ በየአካባቢው እየተደረጉ ካሉ የመርዶ ስነ-ስነርዓቶች መታዘብ እንደሚቻለው፥ የህልፈታቸው ዜና እየተነገረ ካሉት የቀድሞ ታጋዮች መካከል ጥቂት የማይባሉ ዕድሜያቸው በአስራዎቹ መጨረሻ፣ በሃያዎቹ መጀመርያ እና አጋማሽ የነበሩ ወጣቶች፣ ከጦርነቱ በፊት በተለያየ የስራ መስክ አልያም ትምህርት የነበሩ፣ ትግራይ ላይ የተከፈተው ጦርነት ተከትሎ ደግሞ ወደ ሰራዊት የተቀላቀሉ መሆናቸው ያመለክታል።

በትግራይ ክልል ከጦርነቱ ማብቃት አንድ ዓመት ገደማ በኃላ፥ በጦርነቱ ወቅት ከትግራይ ኃይሎች ጋር  ሆነው ሲዋጉ ያለፉት የቀድሞ ታጋዮች የማሰብ፣ መርዶ ለቤተሰቦች የመንገር እና የማፅናናት ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ስነስርዓቶች በሁሉም አካባቢ እየተከወነ ይገኛል።
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ከዛሬ ጀምሮ በጦርነቱ የሞቱትን የቀድሞ ታጋዮች ማንነት እያሳወቀ ነው። ከነገ ጀምሮ ደግሞ በመላው ትግራይ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሐዘን እንደሚታወጅም የክልሉ አስተዳደር አስታውቋል። በጦርነቱ ልጆቻቸውን እና ሌሎች ዘመዶቻቸውን ያጡ ቤተሰቦች ከመርዶ በኃላ ሐዘን ተቀምጠዋል። ምስል Million Haileselasie/DW

ፖለቲካ ምህዳሩ የጠበባት እና ሰላማዊ ትግል የታገደባት ትግራይ ክልልበብሔራዊ የሐዘን ቀኑ እና መርዶ ስርዓት ዛሬ ማምሻውን መግለጫ የሰጡት የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ህዝብ ህልውናው ለማረጋገጥ ከፍተኛ መስዋእትነት ከፍሏል ሲሉ ገልፀዋል። በትግራይ ክልል በኩል በጦርነቱ ያለፉ የቀድሞ ተዋጊዎች ቁጥር ስንት ይሆናል ተብሎ በጋዜጠኞች የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳ፥ አስተዳደራቸው የያለፉት ቁጥር በትክክል እንደሚያውቅ የገለፁ ቢሆንም ለግዜው ግን ይፋ እንደማያደርግ ተናግረዋል። አቶ ጌታቸው "የተሰዉት ቁጥር በሚመለከት ብዙ ተረት ይነገራል። የተሰዉት ቁጥር እንገልፃለን። በዚህ ሰዓት መግለፅ አስፈላጊ ሆኖ አልታየንም። ለትግራይ ህልውና የተከፈለ ዋጋ ልናከብረው፣ የሚገባው ዋጋ ልንሰጠው ልንሰጠው ይገባል ሲባል ለእያንዳንዱ የተሰዋ ቤተሰብ ምስክር ወረቀት ፅፈናል። በሰላም ስምምነቱ ላይ ጥላ ያጠላዉ ጾታዊ ጥቃትስለዚህ ቁጥሩ በእጃችን አለ። ቁጥሩ አሳሳቢ አይደለም፣ ከባድ ዋጋ ከፍለናል። ለህልውናችን የተከፈለ በመሆኑ የሚያስቆጭ ባይሆንም በርካታ ልጆቻችን ከፍለናል" ብለዋል።እነዚህ የቀድሞ ታጋዮች ለማሰብም በርካታ ክልከላዎችን ያሉት ብሔራዊ የሐዘን ቀን ከነገ ጀምሮ በትግራይ እንደሚታወጅ የክልሉ አስተዳደር አስታውቋል። ለዶቼቬለ የተናገሩት የትግራይ ክልል ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ሐላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም ከነገ ጠዋት ጀምሮ በትግራይ የክልሉ ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ ይውለበለባል ብለዋል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ