የቻይና «መቀነትና መንገድ» ምን ይዟል?
ሐሙስ፣ ጥቅምት 8 2016ቻይና የ«መቀነትና መንገድ» የሚል ስያሜ በሰጠችው ግዙፍ ፕሮጀክት 3ኛ ጉባኤ ላይ ለመምከር ባለፈው ሰኞ እና ማክሰኞ የ130 አገሮች መንግስታት እና ተወካዮችና እንዲሁም ከአንድ ሺ በላይ ተሳታፊዎች ቤጂንግ ውስጥ ተገኝተው ነበር ። በጉባኤው ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ፤ የሩስያ ፕሬዚደንት ብላድሚር ፑቲን እና ሌሎችም ተካፍለዋል ።
ቻይና3ኛውን የመቀነትና መንገድ (Road & Belt) ጉባኤ በቢጂንግ ባለፈው ሰኞና ማክሰኞ አካሂዳለች። መቀነትና መንገድ የሚባለው እቅድ እ እ እ በ2013 አም በቻይናው መሪ ሺ ጂፒንግ ተጠንስሶ ወደ ሥራ የገባና፤ ቻይናን ከኢስያ፤ አውሮ፤ አፍሪክና ላቲን አሜሪክ ጋር የሚያገናኝ ሁለገብና ግዙፍ የመሰረተ ልማት ግንባታ ዕቅድ ሲሆን፤ የዘንድሮው ሶስተኛው ጉባኤ የአቅዱን አስረኛ አመትም የሚዘክር እንደሆነ ታውቋል ።
በዘንድሮው ጉባኤ የ130 አገሮችና መንግስታት ተወክዮችና ካንድ ሺ በላይ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን፤ የሩሲያው መሪ ፕሬዝድንት ፑቲን፣ የሀንጋሪውን ጠቅላይ ሚኒስተር ቪክቶር ኦርባንና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስተር አቢይ አህመድ በጉባኤው ከታደሙት 23 የአገር መሪዎች የሚጠቀሱ ናቸው።
ቻይና እስካሁን በመርሀ ግብሩ በበርካታ አገሮች በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወጭ የሆኑባቸው የመንገድ፤ የባብር ሀዲድና የወደብ ግንባታዎችን የገነባች ሲሆን፤ በዚህ ጉባኤም የመርህ ግብሩ የእስካሁን ስኬቶችና የወደፊት ዕቅዶች በሰፈው ተገልጿል።
የቻይናው መሪ ፕሬዝዳንት ሺ ጂፒንግ በጉባኤው ላይ ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር፤ ዘንድሮ አስረኛ አመቱን ያከበረው የመቀነትና መንግድ መርሀ ግብር ዓላማው መሰረተ ልማቶችን በመዘርጋትና በመገንባት ልማትን ማፈጠን፤ ንግድን ማሳለጥና የህዝብ ለህዝብ ግንኑነትን በመፍጠር የዓለምን ኢኮኖሚ ማሳደግ ብሎም አዲስ የዓለማቀፍ የኢኮኖሚ ትብብር መፍጠር ነው፤ በማለት የኢትዮጵያና ቻይና ትብብር አዲስ ምእራፍበዚህ መንፈስም ከኢሮሺያ እስከ አፍርካና ብሎም ላቲን አሜርካ ድረስ ከ 150 አገሮችና 30 አለማቀፍ ድርቶች ጋር የትብብር ሰነድ መፈረሙን አስታውቀዋል።
የህዝቦች የወደፊት እጣ ፈንታ የተጋመደ መሆኑን ያወሱት ፒሬዝዳንት ጂፒንግ፤ የቻይና እድገት የሌላው፤ የሌው እድገትም የቻይና መሆኑንም አንስተዋል። " ቻይና ሊሳካላት የሚችለው አለም ሲሳክለት ነው። ቻይና ስታድግና ሲሳክላትም አለምም ያድጋል ይሳካለታልም። በዚህ የመቀነትና መንገድ የትብብር ማእቀፍ፤ ቻይን በሯን ለዓለም ክፍት ያደረገች ሲሆን፤ በዚህም ዛሬ የቻያና ገበያ ከአለም ገበያ ጋር ሊተሳሰር መቻሉን አብርተዋል፤ አገራቸው ከ140 አገሮች ጋር የንግድና ገበያ ትሥሥር ያላት መሆኑን በመጥቀስ ጭምር። በመጭዎቹ አመታት የመቀነተና መንገድ ትብብር ትኩረቶችን በመዘርዘርም፤ የአየር ንብረት ለውጥና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሚገኙበት መሆኑን አስታውቀዋል።
ጉባኤው በርካታ የሁለትዮሽ ንግግሮችና ውይይቶችም የተካሄዱበት እንደነበር ታውቋል። ከዩክሬኑ ጦርነት በኋላ ካገር ወተው የማይውቁት ፕሬዝዳንት ፑቲን፤ የጉባኤው የክብር እንግዳ በመሆን ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ ከፕሬዝድናት ጂፒንግ ጋር በነበራቸው የሁለትዮሽ ንግግርም፤ በዩክሬኑ ጦርነትና የመካከለኛው ምስራቅ ሁኔታ ላይ እንደተወያዩ ተገልጿል። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አቢይ አህመድም ከጉባኤው ጎንለጎን ከጠቅይ ሚኒስተር ሊኪያዋንግ ጋር በሁለቱ አገሮች የልማትና ኢኮኖሚ ትብብር ላይ መወያየታቸው ታውቋል። የሀንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስተር ቪክቶር ኦርባን ብቸኛው በጉባኤው የተገኙ የአውሮፓ ህብረት አባል አገር መሪ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን፤ የአውሮፓ ህብረት ማዕቀብ ከጣለባቸውና ሄግ በሚገኘው ያለማቀፍ ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት ይፈለጋሉ ከሚባሉት ፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር አብረው በስብሰባ መታደማቸውና መገናኘታቸው በተለይ እዚህ ብራስልስ መነጋገሪያ ሁኗል።
በጉባኤው የተገኙትና ንግግር ይደረጉት የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ ሚስተር አንቶኒዮ ጉቴሬሽ ሶስተኛው የመቀነትና መንገድ ጉባኤ በመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ ትኩረት ማድረጉን አድንቀዋል፤ " የሶስተኝው የመቀነትና መንገድ ጉባኤ እውነታውን አግንቶታል። ያ ለመሰረተ ልማት እድገት የለም። በዚህ በኩል እድገት ከሌለ ደግሞ ለብዙዎቹ ታዳጊ አገሮች አስፈላጊዎቹ መሰረተ ልማቶች ሊኖሩ አይችሉም በማለት የልማት መርሀ ግብሩ ከመንግስታቱ ድርጅት የልማት ግቦች ጋ\ር የሚገናኝ መሆኑን ገልጸዋል። ዋና ጸሀፊው በንግግራቸው መጨረሻም የመክከለኛው ምስራቅ ሁኔታን አንስተው፤ አስቸኳይ የሰባዊ ተኩስ አቁም ስምምነት እንዴረግና እርዳታ እንዲገባ ጥሪ አስተላልፈዋል፤ የጉባኤው ታዳሚዎች መንፈስ ለአካባቢው ስላም ይወርድ ዘንድ እንዲረዳ በመጠየቅ ጭምር ።
ገበያው ንጉሴ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ