1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የነዳጅ እጥረትና የባጃጅ አሽከርካሪዎች አዲስ ስምሪት

ዓርብ፣ ጥር 27 2014

የአፍሪካ ሕብረት በ2063 ተሳክቶ እንዲያየው የሚፈልገውን እና አህጉሩ አንድነቱ ተጠብቆ በልማት የሚራመድበትን ጥቅል ማዕቀፍ አስቀምጧል። ሕብረቱ ይህንን ቢወጥንም የፀጥታ መናጋት አሁንም ዋነኛ የአህጉሩ ፈተና ሆኖ ዘልቋል።

https://p.dw.com/p/46XPi
Äthiopien | Benzinknappheit
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር አገልግሎትና ችግሮቹ

በአማራ ክልል በየጊው ለሚፈጠረው የነዳጅ እጥረት የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅትና የአማራ ክልል መንግስት አንዱ ሌለኛውን ተጠያቂ እያደረጉ ነው፤ ክልሉ የሚላክለትን ነዳጅ ባግባቡ ተቆጣጥሮ ባለመቀበሉ የክልሉ የነዳጅ ድርሻ ወደ ጎረቤት አገሮች በህገወጥ መንገድ እየተሸጠ መሆኑን የነዳጅ አቅራቢ ድርጅቱ አመልክቷል፡፡ በባሕር ዳር ከተማ የሚገኙ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት በበኩላቸው በሚፈጠረው የነዳጅ እጥረት ምክንያት ነዳጅ ለመቅዳት ለሰዓታት ይሰለፋሉ አሊያም በከፍተኛ ዋጋ ለህገወጥ አቅራቢዎች ይዳረጋሉ። 

የአማራ ንግድ ቢሮ በተቻለ መጠን ነዳጅ ወደ ባሕር ዳር ከተማ እንዲገባ እየተደረገ መሆኑን ዛሬ አመልክቷል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በባሕር ዳር ከተማ ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ ለማቃለል ከሳምንቱ መጀመሪያ ጀምሮ ባለሶስት እግር ተሸከርካሪዎች ከዋና ዋና አሰፋልት ውጪ እንዲንቀሳቀሱ ከተማ አስተዳደሩ ወስኗል፡፡

Äthiopien | Benzinknappheit
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

በአማራ ክልል የነዳጅ እጥረት የተለመደና መደበኛ ችግር እየሆነ መጥቷል፡፡ ነዳጅ ለመቅዳት በየነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች እጅግ ረጃጅም የተሸከርካሪ ሰልፎችን ማየትም አዲስ አልሆነም፡፡የጅግሩ መንስኤ ደግሞ የተለያየ እንደሆነ መንግስትና ነዳጅ አቅራቢ ድርጅቱ ይናገራሉ፡፡ የአማራ ክልል ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቀለመወርቅ ምህረቴ እንደሚሉት በየከተሞቹ ያሉ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች ባዶ ናቸው፣ የክልሉ የነዳጅ ኮታም አይታወቅም፡፡

ነዳጅ የሚከፋፈለው እያንዳንዱ ክልል በሚያከናውነው የልማት እንቅስቃሴና ተሸከርካሪ ብዛት እንጂ በኮታ አይደለም ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋናሥራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ኃይለማሪያም ናቸው፡፡ ለነዳጅ አቅርቦት ችግር የአማራ ክልል የነዳጅ ድፖት የሚገነባበት ቦታ ቢጠየቅም ለ10 ዓመታት መልስ መስጠት ባለመቻሉ ነው ይላሉ፡፡ አማራ ክልል ከፍተኛ የነዳጅ አቅርቦት ችግር እንዳለበት ያመኑት ዋና ሠራ አስፈፃሚው፣ ከልሉ የሚላክለትን የነዳጅ ፍጆታ ተከታትሎ ስለማይቀበል ነዳጁ ወደ ኬንያ፣ ሶማሌላንድ፣ኬንያና ኤርትራ በህገወጥ መንገድ እንደሚሽጥ አረጋግጠዋል፡፡

በቅርቡ ወደ ቦታው መመደባቸውን ያመለከቱት የንግድ ቢሮ ኃላፊው አቶ ቀለመወርቅ፣ከመሬት ጋር የተያያዘውን ጉዳይ እንደማያውቁና በቀጣይ አስፈላጊው ሁሉ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡ በአማራ ንግድ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አብዮት ምህረት ዛሬ እንደተናገሩት ነዳጅ አሁን እየገባ መሆኑን ጠቁመው በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት ግን ውይይቶች ከባለድርሻ አካላት ጋር ይቀጥላል ብለዋል፡፡

Äthiopien | Benzinknappheit
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

በባሕር ዳር ከተማ ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመፍታት ባለሶስት እግር ተሸከርካሪዎች ከዋና አሰፋልት ውጭ እንዲንቀሳቀሱ ሰሞኑን መወሰኑን ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ በትግሉ ተስፋሁን ተናግረዋል፡፡ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴም በክልሉ በኩል ያሉ ችግሮች እንደሚፈቱ አረጋግጠዋል፡፡ የባለ ሶስት እግር ተሸከርካሪ ሾፌር የሆነው አወቀ ነጋ ነዳጅ ለመቅዳት እስከ 8 ሰዓት እንደሚጠብቅ ከጥቁር ገበያ ደግሞ አንድ ሊትር እስከ 70ና 80 ብር እንደሚገዛ ተናግሯል፡፡ በባህር ዳር ከተማ የኦይል ሊቢያ ነዳጅ ማደያ ሰራተኛ ታደሰ ዓለም ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት እንዳለ አመልክቷል፡፡ በአማራ ክልል 300 ያህል ነዳጅ ማደያዎች ቢኖሩም ብዙዎቹ የሚገዙትን ነዳጅ በማጠራቀሚያ ጋን ሳያስገቡ በአየር ላይ እንደሚሸጡት ከነዳጅ አቅራቢ ድርጅቱ ማረጋገጥ ችለናል፡፡

ዓለምነው መኮንን

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ