የአውሮጳ ባለሥልጣናት የኢትዮያ ጉዞ አንደምታ
ሐሙስ፣ ጥር 4 2015ማስታወቂያ
የጀርመን እና የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ ይገኛሉ። ሚንስትሮቹ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ከቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚንሥትር ቺን ጋንግ ጉብኝት አንድ ቀን በኋላ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፈረንሳይ የአውሮፓ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካትሪን ኮሎንና እና ከጀርመን የፌደራል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ባየርቦክ ጋር እንደተነጋገሩ እና በመግለጥ ውይይታቸው «ጥልቅ እና ፍሬያማ» እንደሆነ ገልጠዋል። «ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ እና ከጀርመን ጋር ያላትን ጠንካራ እና የቆየ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው»ም ብለዋል።
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ነበሩ። እንደሚታወቀው ፣ቀደም ሲል ደግሞ የታላቁዋ ብርታኒያ ተጠሪ‐የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አዲስ አበባን ጎብኝተዋል።
አሁን ደግሞ፣ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የጀርመንና የፈረንሣይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ኢትዮጵያ ገብተዋል። ይህ ምንን ያመለክት ይሆን?
ይልማ ኃይለ ሚካኤል/ካይት ወከር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ