የእነ አቶ ጃዋር መሃመድ የህክምና ክርክር
ሐሙስ፣ የካቲት 18 2013ማስታወቂያ
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብር እና ሐገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አላከበሩም ያላቸዉን የወሕኒ ቤት ኃላፊዎችን ዛሬ ለጥያቄ ጠርቷል፡፡ፍርድ ቤቱ የወሕኒ ቤት ኃላፊዎችን የጠራዉ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የታሰሩት አቶ በቀለ ገርባ ባለፈዉ የካቲት 11፣ ከፍርድ ቤቱ በተሰጣቸው ፍቃድ መሰረት ወደሚታከሙበት የግል ሐኪም ቤት ሲሔዱ ወደማይፈልጉት የመንግሥት ሆስፒታል ተገደዉ በመወሰዳቸዉ ሰበብ ነዉ።ከተከሳሽ ጠበቆች አንዱ እንዳሉት ዛሬ ችሎት የቀረቡት የማረሚያ ቤቶች ረዳት ኮሚሽነር ግርማ አደሬ ለችሎቱ ጥያቄ በሰጡት መልስ የፀጥታ ሥጋትን ምክንያት አቅርበዋል።ሕዝብን በማጋጨት ሙከራና በሌሎች ተያያዥ ወንጀሎች ተጠርጥረዉ የታሰሩት የኦሮሞ ፖለቲከኞች የሕክምና ሥፍራና የሐኪሞቻቸዉ ማንነት እያወዛገበ ነዉ።
ስዩም ጌቱ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ