1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእነ አቶ ጃዋር የክስ ሂደት

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 6 2014

 በእነ አቶ ጃዋር መሃመድ የክስ መዝገብ የተጠቀሱ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) አመራሮች በሌሉበት  ምስክሮችን የማድመጥ ሂደት  እንዳይጀመር በጠበቆቻቸው የቀረበውን ጥያቄ  ጠቅላይ አቃቤ ህግ በመቃወም መልስ ሰጠ፡፡

https://p.dw.com/p/44JV4
Äthiopien Jawar Mohammed
ምስል Tiksa Negeri/Reuters

በእነ አቶ ጀዋር መሀመድ የክስ መዝገብ ላይ የጠበቆችን አቤቱታ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተቃውሟል

የእነ አቶ ጃዋር የክስ ሂደት ምስክር የመስማት ሂደት እና ተቃውሞው

 በእነ አቶ ጃዋር መሃመድ የክስ መዝገብ የተጠቀሱ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) አመራሮች በሌሉበት  ምስክሮችን የማድመጥ ሂደት  እንዳይጀመር በጠበቆቻቸው የቀረበውን ጥያቄ  ጠቅላይ አቃቤ ህግ በመቃወም መልስ ሰጠ፡፡

ዛሬ በአዲስ አበባ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በተሰየመው ችሎት መልሱን ያቀረበው አቃቤ ህግ ተከሳሾቹ በተከሰሱበት ክስ ላይ ለመከራከር በአካል ፍርድ ቤት የመገኘት መብታቸውን በራሳቸው ፍላጎት በመተዋቸው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክሱን በሌሉበት ለማየት የወሰነው ውሳኔ ህጋዊ ነው ብሏል፡፡

የተከሳሾች ጠበቆች የከፍተኛ ፍርድ ቤት እነ አቶ ጃዋር በሌሉበት በግልጽ ችሎት የምስክሮች አሰማም ሂደቱ እንዲጀምር የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማለት ይሁኝታ አግኝተው ነበር፡፡

ስዩም ጌቱ 

ታምራት ዲንሳ 

አዜብ ታደሰ