የከረዩ አባገዳዎች ግድያ፣ ዕርቅና የኢሰመኮ ስጋት
ሐሙስ፣ መጋቢት 15 2014ማስታወቂያ
የከረዩ አባገዳ አባላት በመገደላቸዉ ሰበብ የተፈረዉን ጠብና ቅሬታ በእርቅ ለመፍታት የሚደረገው ጥረት የሕግ ተጠያቂነትን ሊያደናቅፍ እንደማይገባ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ፡፡የመንግስት ፀጥታ አስከባሪዎች ባለፈዉ ታሕሳስ በርካታ የከረዩ አባገዳ አባላትና ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸዉን የተለያዩ ምንጮች ዘግበዋል።ግድያዉ ያስከትላል የተባለዉን ጠብ ለማስወገድ ጉዳዩ በእርቅ እንዲያበቃ ሽምግልና ተይዟል።የግድያዉን መንስኤና የገዳዮችን ማንነት የመረመረዉ ኢሰመኮ ጠብና ቅሬታዉን በእርቅ ለመፍታት የሚደረገዉን ጥረት እንደሚደግፍ አስታዉቋል።ይሁንና ኮሚሽኑ እንዳለዉ እርቁ በወንጀል ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሚደረገዉን ሒደት የሚያስቀር መሆን የለበትም።ሽምግልናዉን የሚመሩት የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት ዋና ፀኃፊ አባገዳ ጎበና ሆላ ግን፣ የከረዩ ገዳ ሚቺሌ ዱላቻ ማህበረሰብ አባላት የተዘረፉት ተመልሶላቸው ካሳ እንዲከፈላቸው መስማማታቸውን አመልክተዋል፡፡
ስዩም ጌቱ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ