1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የከተራ ክብረ በዓል በአዲስ አበባ

ሰለሞን ሙጬ
ቅዳሜ፣ ጥር 10 2017

14 ታቦታተ ሕግ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው በጃን ሜዳ የሚያድሩ ሲሆን ጃን ሜዳ ለክብረ በዓሉ በጥሩ ሁኔታ መዘጋጀቱን ተመልክተናል። ምዕመኑም የባህል አልባሳትን ለብሶ በእልልታ፣ በዝማሬ ታቦታቱን አጅቦ የሥነ ሥርዓቱ ድምቀት ሆኗል።

https://p.dw.com/p/4pK5d
Äthiopien Addis Abeba 2025 | Feier des äthiopischen Epiphaniasfestes
ምስል Solomon Muche/DW

ከተራ በአዲስ አበባ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የአደባባይ በዓል የሆነው የከተራ በዓል በአዲስ አበባ ዛሬ ቅዳሜ ጥር 10 ቀን መንፈሳዊ ወጉን ጠብቆ ተከብሯል።

ለዚሁ ለከተራ እና ለጥምቀት ክብረ በዓላት የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች፣ አደባባዮች፣ አብያተ ክርስትያናትን እና ቅጥራቸው በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ትዕይንተ መገለጫዎች ተውበዋል።

14 ታቦታተ ሕግ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው በጃን ሜዳየሚያድሩ ሲሆን ጃን ሜዳ ለክብረ በዓሉ በጥሩ ሁኔታ መዘጋጀቱን ተመልክተናል።

ምዕመኑም የባህል አልባሳትን ለብሶ በእልልታ፣ በዝማሬ ታቦታቱን አጅቦ የሥነ ሥርዓቱ ድምቀት ሆኗል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ ጥር 10 እና 11 ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮርዳኖስ ወንዝ ወርዶ ለሰው ልጆች ሁሉ ፀጋን ለመስጠት መጠመቁን ለማስታወስ የከተራን እና የጥምቀት መንፈሳዊ ክብረ በዓላትን ታከብራለች። 14 ታቦታት ለዚሁ ሲባል ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው ወደ ጃን ሜዳ ሄደው ያድራሉ።

በዓለም የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኒስኮ) የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበው የጥምቀት በዓል በዋዜማው ዛሬ የከተራው ኹነት ልዩ በሆነ ድምቀት ተከናውኗል
በዓለም የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኒስኮ) የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበው የጥምቀት በዓል በዋዜማው ዛሬ የከተራው ኹነት ልዩ በሆነ ድምቀት ተከናውኗልምስል Solomon Muche/DW

በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ ታቦታት በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ውኃ የሚገኝበት ሥፍራ ወይም ወንዝ የሚወርዱ ሲሆን መስህብ በሆኑት ልዩ ልዩ የቤተ ክርስትያኗ መንፈሳዊ ዝማሬዎች፣ የምእመኑ እጀባ ወጥተው በድንኳን ውስጥ እንዲያድሩ ይደረጋል። ያነጋገርነቸው ቀሲስ ሙሉጌታ ስዩም በቤተ ክትስትያን የሚያገለግሉ ሲሆን የበዓሉን መታሰቢያ ትርጉም ነግረውናል።

በአዲስ አበባ ከተማ 74 ጥምቀተ-ባህራት መኖራቸውን የቤተ መረጃ ይጠቁማል።

በዓለም የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኒስኮ) የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበው የጥምቀት በዓል በዋዜማው ዛሬ የከተራው ኹነት ልዩ በሆነ ድምቀት ተከናውኗል።

ምዕመኑም የባህል አልባሳትን ለብሶ በእልልታ፣ በዝማሬ ታቦታቱን አጅቦ የሥነ ሥርዓቱ ድምቀት ሆኗል።
ምዕመኑም የባህል አልባሳትን ለብሶ በእልልታ፣ በዝማሬ ታቦታቱን አጅቦ የሥነ ሥርዓቱ ድምቀት ሆኗል።ምስል Solomon Muche/DW

ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች ታላቅ በረከት የሚያገኙበት ይህ በመላ ሀገሪቱ የሚከናወን ክብረ በዓልየኢትዮጵያ መገለጫ ሐብት ጭምር ነው። ቀሲስ ሙሉጌታ ስዩም በዓሉ ቤተ ክትስትያኗ ባለችበት ሁሉ የሚከበር መሆኑን ጠቅሰዋል።

መንግሥት ለዚህ ዓለም አቀፍ መስህብ የሆነ ክብረ በዓል ጥበቃ እንደሚያደርግ አስቀድሞ ያስታወቀ ሲሆን ጥብቅ ጥበቃ እና ፍተሻ ሲደረግም አስተውለናል።

ለዚሁ ለከተራ እና ለጥምቀት ክብረ በዓላት የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች፣ አደባባዮች፣ አብያተ ክርስትያናትን እና ቅጥራቸው በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ትዕይንተ መገለጫዎች ተውበዋል።

ሰሎሞን ሙጬ

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር