1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

የፕሬዝዳንት ትራምፕ የዩክሬንን ጦርነት የማስቆም ዕቅድ

ረቡዕ፣ ጥር 7 2017

ተመራጭ ፕሬዝዳንት ትራም እራሳቸውም ሰኞ እለት ለአንድ ሜዲያ በሰጡት አስተያየት ፕሬዝዳንት ፑቲንም ከሳቸው ጋር መገናኛኘቱን እንደሚፈለጉትና ከሰኞው በዓለ ሹመት በሗላ እንደሚገናኙ ያላቸው እመነት በመግለጽ ይህ ሁለቱንም በተለይም ዩክሬንን እያወድመ ያለ ጦርነት ባስችኳይ መቆም እንድላበት እንደሚያምኑ አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/4pAdz
የአሜሪካዉ ተመራጭ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የፊታችን ሰኞ የፕሬዝደንትነቱን ስልጣና ከተረከቡ በኋላ ከሩሲያዉ አቻቸዉ ቭላድሚር ፑቲን ለመነጋገር አቅድዋል
የዩናይትድ ስቴትሱ ተመራጭ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ።በምርጫ ዘመቻቸዉ ወቅት በገቡት ቃል መሠረት የሩሲያና የዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም ከሩሲያዉ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለመነጋገር አቅደዋል።ምስል Evan Vucci/AP/picture alliance

የፕሬዝዳንት ትራምፕ የዩክሬንን ጦርነት የማስቆም ዕቅድ

የፊታችን ሰኞ የዩናይትድ ስቴትስን የፕሬዝደንትነት ሥልጣን የሚረከቡት ተመራጭ ፕረዝዳንት ዶናልድ ትራም  ከሩሲያው አቻቸው ከቭላድሚር  ፑቲን ጋር ፊትለፊት ተገናኝተው የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት ስለሚያበቃበት  ሁኔታ እንደሚወያዩ  ሰሞኑን ከዋሽንግተንና ከሞስኮ የወጡ መርጃዎች ይፋ አድርገዋል።የተሰናባቹ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን መስተዳድርና የአዉሮጳ ተባባሪዎቹ ለዩክሬን መንግሥት ከፍተኛ ወታደራዊ ድጋፍ እየሰጡ ነዉ።ትራምፕ ግን ሶስት ዓመት ያስቆጠረዉን ጦርነት እንደሚያስቆሙ በምርጫ ዘመቻቸዉ ወቅት ቃል ገብተዋል።

 

የፕሬዝዳንት ትራምፕ የዩክሬንን ጦርነት የማስቆም ጅማሮ

የፊታችን ሰኞ ዳግም ወደ ስልጣን የሚመጡት የአሜሪካ ተመራጭ ፕረዝዳንት ዶናልድ ትራም በቅርቡ ከሩሲያው አቻቸው ፕሬዝድንት ፑቲን ጋር ተገናኝተው ሶስት አመት የዘለቀው የሩሶያ -  ዩክሬን ጦርነት ስለሚያበቃበት  ሁኔታ እንደሚወያዩ  ሰሞኑን ከዋሽንግተንና ሞስኮ የወጡ መርጃዎች ይፋ አድርገዋል።

 ፕሬዝዳንት ትራምፕ በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት ከተመረጡ፤ ሳይውሉ ሳይድሩ አገራቸውን ለከፍተኛ ወጭ፤ አውሮፓንና ሌላውንም ለጦርነት ስጋት የዳረገውን የሩሲያና ዩክሬንን ጦርነት እንደሚያስቆሙ አጽናኦት ስተው ሲናገሩ የነበር መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፤ ስራ በጀመሩ ጥቂት ቀናት ውስጥም ክፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ተገናኝተው የሚወያዩ መሆኑን በቀጣይ የፕሬዝዳንት ትራም የጸጥታ አማካሪ የሚሆኑት ሚስተር ሚከ ዋትዝ አረጋግጠዋል፤ “ የሰበሰባውን አክሄድና ይዘት ገና በትክክል ያስቀመጥን ባይሆንም እየሰራንበት ነው” በማለት በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ከሞስኮ ጋር የስልክ ልውውጥ እነንደሚኖርም አስታውቀዋል።

ተመራጭ ፕሬዝዳንት ትራም እራሳቸውም ሰኞ እለት ለአንድ ሜዲያ በሰጡት አስተያየት ፕሬዝዳንት  ፑቲንም ከሳቸው ጋር መገናኛኘቱን እንደሚፈለጉትና ከሰኞው በዓለ ሹመት በሗላ እንደሚገናኙ ያላቸው እመነት በመግለጽ ይህ ሁለቱንም በተለይም ዩክሬንን እያወድመ ያለ ጦርነት ባስችኳይ መቆም እንድላበት እንደሚያምኑ  አስታውቀዋል።

የትራምፕና ፑቲን መገናኛ የት ይሆን?

በተመሳሳይ ሁኔታ ክሞስኮም የውይይት ፍላጎት ያለ መሆኑም ተገልጿል። ሆኖም ግን የስብሰባው ቦታና አስተናጋጁ አገር ገና እንዳልተወሰነ ነው የሚነገረው። ፕሬዝዳንት ፑቲን ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ዘሄግ በሚገኘው አለማቀፉ የወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ የወጣባቸው በመሆኑ የሜሂዱባቸው አገራት በፍርድ ቤቱ ማቋቋሚያ የሮም ስነድ መሰረት አሳልፈው የማይሰጧቸው ስለመሆኑ መረጋገጥ ይኖርበታል። እስካሁን ሰርቢያ የሮሙን ሰነድ ፈራሚ ባለመሆኗና በጦርነቱም ገለልተኛ ሆና የቆየች በመሆኑ የትራምፕንና ፑቲንን ስብስባ ለማስተናገድ ፈቃደኛ ብቻ ሳትሆን ምቹም መሆኗንና ፕሬዝዳንቱ ሚስተር አሌክሳንደር ቩሲ በመገናኛ ብዙሀን ሲናገሩ ተሰምተዋል። ስዊዘርላንድ በበኩሏ ምንም እንኳ የሮሙን የአለማቀፍ ፍርቤት  ቤት  ማቁቋሚያ ስነድ የፈረመች ቢሆንም፤ ለሰላም ሲባል አገራቸው ለፕሬዝዳንት ፑቲን ዋስትና የምትሰጥበት የህግ አግባብ እንዳለ በመግለጽ ስብሰባውን እንደምታስተናግድ ቀደም ሲል አስታውቃለች። በመሆኑም ምናልባትም ስብሰባው በሲዊዘርላንድ ሳይካሄድ አይቀርም እየተባለ ነው።

ትራምፕ አሁን ሥልጣን ከያዙ በኋላም ከፑቲን ጋር ለመነጋገር ማቀዳቸዉን የሁለቱም ሐገራት ባለሥልጣናት አስታዉቀዋል።
ትራምፕ በመጀመሪያዉ ዘመነ-ሥልጣናቸዉ ወቅት ከሩሲያዉ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተዉ ተነጋግረዉ ነበር።ምስል Newscom World/IMAGO

ታስቢ የድርድር ነጥቦችና ተቀባይነታቸው

የስብሰባውን አካሄድና የመደራደሪያ ነጥቦችን በሚመለክት የፕሬዝዳንት ትራም ባለሙያዎች እየሰሩበት መሆኑ ተገልጿል።  የፕሬዝዳንት ትራም ቀጣይ የዩክሬን ልዩ መልዕክተኛ ጀነራል ኬይትዝ ኮሎግ ሲናገሩ እንደተሰሙት “የፒረዝዳንቱ አላማ ሁሉንም ነገር ለሩሲያ ለመስጠት ሳይሆን፤ የዩክሬንንም አንድነትና ሏአላዊነት ማስጠበቅ ነው”። ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር በሚኖረው ድርድር ጦርነቱን ባለበት ሁኒታ ማስቆም አስፈላጊ ቢሆንም እንኳ፤ የዩክሬን ደህንነትና ሉላዊነት ዋስትና የሚያገኘው ግን የኔቶ አባል በመሆነ ብቻ እንደሆነ ሲያሳስቡና ሲጠይቁ  ቆይተዋል። ሆኖም ግን ፤ የዩክሬን የኔቶ አባልነት ጥያቄ  በሩሲያ በኩል የደህንነት ስጋት የሜነሳበትና ተቀባይነት ሊኖረው የማይችል ቀይ መስመር እንደሆነ ነው ታዛቢዎች የሚናገሩት። በአሁኑ ወቅት የዩክሬን አንድ አምስተኛ ምስራቃዊ ግዛቶች በሩሲያ ቁጥጥር ሰር ሲሆኑ፤ የትራምፕ የሰላም ሀሳብ ጦርነቱ ባለበት እንዲቆም፤ የዩክሬን የኔቶ አባልነት ጥያቄ እንዲዘገይና የአውሮፓ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሀይል በአገሪቱ እንዲሰፍር የሚጠይቅ መሆኑ ተስምቷል። ይህ ግን በሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች ብቻ ሳይሆን በጦርነቱ በተዘዋዋሪም ቢሆን በመሳተፍ ላይ ባሉት ብዙዎቹ  ያውሮፓ አገሮች ተቀባይነት እንደሌለው የሚነገር ሲሆን፤ ይህም የፕሬዝዳንት ትራምፕን የሽምግልናና ሰላም የማውረድ ጥረት አስቸጋሪ እንደሚያደርገው ነው የሚጠበቀው።

ከፊት ለፊትና ከግራ ወደ ቀኝ የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮልድሚየር ዘለንስኪና የዩናይትድ ስቴትሱ ተመራጭ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ።መስከረም 2024 (ዝግአ)
ከፊት ለፊትና ከግራ ወደ ቀኝ የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮልድሚየር ዘለንስኪና የዩናይትድ ስቴትሱ ተመራጭ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ።መስከረም 2024 (ዝግአ)ምስል Alex Kent/Getty Images

ለትራምፕ የሰላም ጥረት መሳካት የሚሰሙ መልካም ምኞቶች

በአሁኑ በበርካታ አካባቢዎች ጦርነቶች እየተካሂዱ ባለበት ወቅት፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህንን አደገኛ ጦርነት ለማስቆም ተነሳሽነት ማሳየታቸውንና እርምጃም ለመውሰድ እንቅስቅሴ መጀመራቸውን  ግን ብዙዎች በማድነቅ እንዲሳክላቸውም ምኞታቸውን እየገለጹ ነው።  በመዕራብ አውስትርሊያ- ፐርዝ  የከርቲን ዩንቨርሲቲ የአለም አቀፍ ግንኙነት ፕሮፌሰር የሆኑት ፕሮፌሰር  ጆ ሲራውሳ፤ ይህንን የፕሬዝዳንት ትራምፕን ተነሳሽነት እ እ እ በ1962 ዓማ ፒሬዝዳንት ኬኔዲ ከያኔው የሶቭይት ህብረቱ መሪ ክሩስቼቭ ጋር በመገናኘት አንዣቦ የነበረውን የኒውክለር ስጋት ለማስወገድ  ከወሰዱት እርምጃ ጋር በማመሳሰል ጥሩ ጅማሮ፤ በማለት አድንቀውታል ።

ገበያው ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ