1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እየሰፋ የመጣው የባንኮች እና የትይዩ ገቢያ የውጪ ምንዛሪ ግብይት

ሥዩም ጌቱ
ሐሙስ፣ ጥር 8 2017

በኢትዮጵያ ከማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ ወዲህ እየጠበበ የመጣው ባንኮችና በተለምዶ ጥቁር ገቢያ ተብሎ የመሚታወቀው የትይዩ ገቢያ የውጪ ምንዛሪ መጠን አሁን አሁን ዳግም የሰፋ ልዩነት ማሳየት ጀምሯል፡፡ ከሳምንታት በፊት በትይዩ ገቢያው እና የባንኮች የውጪ ምንዛሪ መጠን መካከል የነበረው የ10 ብር ግድም ልዩነት አሁን ወደ 25 ብር መስፋቱ ተነግሯል፡፡

https://p.dw.com/p/4pErM
እየሰፋ የመጣው የባንኮች እና የትይዩ ገቢያ የውጪ ምንዛሪ ግብይት
እየሰፋ የመጣው የባንኮች እና የትይዩ ገቢያ የውጪ ምንዛሪ ግብይት ምስል Solomon Muchie/DW

የባንኮች እና የትይዩ ገቢያ የውጪ ምንዛሪ ግብይት መጠን መስፋት

በኢትዮጵያ ከማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ ወዲህ እየጠበበ የመጣው ባንኮች እና በተለምዶ ጥቁር ገቢያ ተብሎ የመሚታወቀው የትይዩ ገቢያ የውጪ ምንዛሪ መጠን አሁን አሁን ዳግም የሰፋ ልዩነት ማሳየት ጀምሯል፡፡

ከሳምንታት በፊት በትይዩ ገቢያው እና የባንኮች የውጪ ምንዛሪ መጠን መካከል የነበረው የ10 ብር ግድም ልዩነት አሁን ላይ ወደ 25 ብር መስፋቱ ተነግሯል፡፡

የምንዛሪ መጠን ልዩነቱ መስፋት ኢትዮጵያ ባለፈው ሃምሌ ወር ይፋ ያደረገችውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን አንዱና ዋነኛ ግብ እንዳይፈትንም ያሰጋል ነው የተባለው፡፡

በኢትዮጵያ የትይዩ ገቢያው የውጪ ምንዛሪ ተመንአለመረጋጋቱን ቀጥሎበታል፡፡ ከቀናት በፊት አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ130 ብር ይመነዝር የነበረው ትይዩ ገቢያው አሁን ላይ አንዱን የአሜሪካ ዶላር በ150 ብር ከፍ በማድረግ የብርን የመግዛት አቅም ይበልጥ አድክሞታል፡፡ ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች ልዩነቱን ለማጥበብ ለወራት ስሰሩበት የነበረውን ልዩነት ዳግም የሚያሰፋ ተግባር ሆኖም ታይቷል፡፡ በተለምዶ የዶላር ጥቁር ገቢያ ተብለው የሚታወቁት መሰል ተለዋዋጭነትን ሲያሳዩ በኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች አሁን ላይ ረዘም ላለ ጊዜ አንዱ ዶላር በ124 ብር ገደማ ይመነዘራል፡፡ ይህ የትይዩ ገቢያው የዋጋ ተመን አለመረጋጋት አገሪቱ ከወራት በፊት ባለፈው ሃምሌ ወር ላይ ወደ ተግባር ያስገባችውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን ውጥን እንዳይፈትንም አስግቷል፡፡

 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ
በሀገሪቱ የተፈጠረውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የነበረው የምንዛሬ ክፍተት ጠቦ የነበረ ቢሆንም፤በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የንግድ ባንኮች ያለው ልዩነት ወደ 25 ብር ከፍ ብሏል።ምስል Eshete Bekele/DW

በዩናይትድ ኪንግደም የፋይናንስ አስተዳደር ባለሙያ ሆነው የሚሰሩት አብዱልመናን መሃመድ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲውዋነኛው ትኩረት ይህ በንግድ ባንኮች እና ትይዩ ገቢያ መካከል ያለውን የውጪ ምንዛሪ መጠንን ማጥበብ እንደሆነ በማንሳት፤ ነገሩ ለአዲሱ ፖሊሲ ፈታኝ ሊሆን የሚችል ብለውታል፡፡ “ልዩነቱ ለምን ሰፋ ብለን ስንጠይቅ የውጪ ምንዛሪ ስርዓት ማሻሻያው ፍቱም ምሉዕ ባለመሆኑ ነው” የሚሉት ባለሙያው የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለካረንት እንጂ ለካፒታል ገቢያ እልባት ስላላመጣ ጥቁር ገቢያውን ማትፋት እንዳልተቻለ አስረድተዋል፡፡

ተረጋግቶ የቆየው የባንኮች እና ትይዩ ገቢያው የውጪ ምንዛሪ መጠን ድንገት አሁን ለምን አገረሸ ለሚለውም ባለሙያው ሁለት መላምቶችን ያስቀምጣሉ፤ “አንዱ ምናልባት ከህዳር ወር እስከ መጋቢት ግድም ድረስ የገቢው እንቅስቃሴ በተለይም ወደ ውጪ የሚደረግየውጪ ምንዛሪ ፍላጎት ከፍ የሚልበት ወቅት መሆኑ ሲሆን ሌላኛው ምክንያት ደግሞ በቅርቡ ብሔራዊ ባንክ የባንኮች የማበደር መጠን ከ14 ወደ 18 በመቶ ከፍ እንዲል ማድረጉ ከፍ ያለ ገንዝብ ወደ ገቢ እንዲረጭና የውጪ ምንዛሪ ፍላጎቱን ልያንር ይችላል የሚል ነው” ብለዋል፡፡ እናም ነገሮች በዚህ ከቀጠሉ ልዩነቱ ይበልጡንም ሊሰፋ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡

ባንክ ላልሆኑ የግል ተቋማት ፈቃድ ተሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ግዢ እና ሽያጭ እንዲያከናውኑ ባንክ ላልሆኑ የግል ተቋማት ፈቃድ ሰጥቶ ነበር።የተወሰኑትም ሥራ ጀምረዋል።ምስል Solomon Muchie/DW

እናም ይላሉ ባለሙያው የሰፋው የትይዩ ገቢያ እና ባንኮች የምንዛሪ መጠን ቀጣይነት ካለው አደጋ ልኖረው እንደሚችል አስረድተዋል፡፡ “እንደዚህ የሚቀጥል ከሆነ ልዩነቱ መንግስት በንግድ ባንክ በኩልም ብሆን ልዩነቱ እንዲጥብ ባንኮችን ያበረታታል ተብሎ ይጠበቃል” ያሉት ባለሙያው ልዩነቱ እየሰፋ የሚመጣ ከሆነ ህጋዊውን የምንዛሪ መንገድ የሚጠቀሙ እንደተለመደው እየቀነሱ ልመጡ ነው፡፡ ባንኮች አንድ ከፍተኛ የሆነ እርምጃ የሚወስዱ ከሆነ ደግሞ ኢኮኖሚውን ይበልት ልጎዳው ይችላል፡፡

ወደ ገቢያው የሚረጨውን ገንዝብ መቀነስ መንግስት ግሽበቱን ሚቆጠጣጠርበት አንዱ መንገድ ልሆን እንደምችልም ባለሙያው በአስተያየታቸውን ገልጻዋል፡፡

ሥዩም ጌቱ

አዜብ ታደሰ

ፀሀይ ጫኔ