1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኦሮሚያ ክልል አሙሩ ወረዳ ልጆቻቸው ወደ ታጣቂዎች ተቀላቀሉ የተባሉ 17 ሰዎች ታሰሩ

ነጋሳ ደሳለኝ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 22 2017

በአሮሚያ ክልል አሙሩ ወረዳ “ልጆቻችሁ ታጣቂዎች ተቀላቅለዋል” በሚል 17 ሰዎች መታሰራቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ 7 ወራት ታስረው የተፈቱ የ75 ዓመት አረጋዊ በተመሳሳይ ክስ ድጋሚ መታሰራቸውን ልጃቸው ገልጸዋል። የአሙሩ ወረዳ አስተዳዳሪ “ቤተሰብ ልጆቹን እንዲያመጣ በተቀመጠ አቅጣጫ” የታሰሩ መኖራቸውን ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል

https://p.dw.com/p/4oht6
የአሙሩ ወረዳ
የአሙሩ ወረዳ በግጭት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባት ነችምስል DW

በኦሮሚያ ክልል አሙሩ ወረዳ ልጆቻቸው ወደ ታጣቂዎች ተቀላቀሉ የተባሉ 17 ሰዎች ታሰሩ

በሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ልጆቻቸው ከታጣቂዎች ጋር ተቀላቅለዋል የተባሉ 17 ሰዎች መታሰራቸውን የታሳሪ ቤተሰቦች ለዶቼ ቨለ ተናገሩ።  ሰዎቹ የታሰሩት “[ልጆቻችሁ] ወደ ታጣቂዎች ተቀላቅለዋል፣ አምጡ” ተብለው እንደሆነ ያነጋርናቸው ሁለት የታሳሪ ቤተሰብ አባላት አመልክተዋል፡፡ 

በወረዳው ለሰባት ወራት ያህል ያለ ፍርድ ታስረው ከነበሩ አርሶ አደሮች መካከል የተወሰኑት በህዳር ወር 2017 ዓ.ም ተለቅቀው የነበረ ሲሆን “ልጆቻቹ ከጫካ አልተመለሱም” ተብለው ድጋሚ የታሰሩ ሰዎች መኖራቸውን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

በግጭት ክፉኛ ተጎቶ የነበረው የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ 130 የሚደርሱ ሰዎች በወረዳው ለ7 ወራት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ታስረው መቆየታቸውን ጥቆማ እንደደረሰው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባለፈው ህዳር ወር መጀመሪያ ላይ ገልጿል፡፡ እነዚህ የታስሩ ሰዎች አብአዛኞቹ አርሶ አደሮች ሲሆኑ “ልጆቻችሁ በአካባቢው ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ጋር ተቀላቅለዋል እና መልሷቸው” በሚል እንደታሰሩ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የታሳሪ በተሰብ ተናግረዋል፡፡

 በአሙሩ ወረዳ የሚደርሱ ጥቃቶች መበራከት

ከታጣቂዎች ጋር ተቀላቅለዋል የተባሉ ወጣቶችም ዕድሜያቸው እስከ 25 የሚደርሱና ከቤተሰብ ጋር ከተለያዩ ረጅም ጊዜ በመሆኑ ልጆቹን ማግኘትና መመለስ አለመቻላቸውን አንድ አባታቸው በአሙሩ ፖሊስ ጣቢያ ድጋሚ መታሰራቸውን የነገሩን ነዋሪ ገልጸዋል፡፡ አባታቸው በ75 ዓመታቸው በፖሊስ ጣቢያ ከዚህ ቀደም ለ7 ወራት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ታስረው ከቆዩ በኋላ እንደገና ልጃችሁ ባለመመለሱ ፖሊስ ጣቢያ መቆየት አለባችሁ ተብለው እንደታሰሩ ገልጸዋል፡፡

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ፦ ምስል ከማኅደር
ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ከመንግሥት ጋር በገጠመው ውጊያ ባለፉት ዓመታት በኦሮሚያ ክልል ብርቱ ሰብአዊ ጉዳት ደርሷል። ምስል Negasa Desalegn/DW

“ፖሊስ ጣቢያ ነው ተቀመጥው ያሉት፡፡ አንድ ሰው ወንጅል ከሰራ በሰራው ወንጀል በሀገሪቱ ህግ መጠየቅና ኃላፊነት መውሰድ አለበት በሚለው እናምናለን፡፡ እነዚህ ግን ምንም ውሳኔ አላገኙም፡፡ የ75 ዓመት ሽማግሌን ዕድሜው ከ25 ዓመት በላይ ለሆነው ልጅ ኃላፊነት ውሰድ ተብሎ 8 እና 9 ወራት ፖሊስ ጣቢያ ያለ ምንም ፍርድ ማስቀመጥ የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው” ብሏል፡፡

በቅርቡ ከአንድ መንደር 17 ሰዎች ታስረዋል

በአሙሩ ወረዳ በተሰባቸው ከታሰሩት መካከል ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ሌላው ነዋሪ በቅርቡ እናትና አባታቸው መታሰራቸውን አመልክተዋል፡፡ በተሰቡም በተመሳሳይ ከታጣቂዎች እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ አንድ ልጃችሁ ሽፍተዋል ተብሎ መታሰራቸውን በስልክ ተናግረዋል፡፡ በተሰባቸውን ጨምሮ ከእሳቸው መንደር 17 ሰዎች ሰሞኑን መታሰራቸውን የተናገሩት ነዋሪው ወደ ታጣቂዎቸ ተቀላቅለዋል የተባለው ወንድሙ ለጊዜ የት እንዳለ እንደማውቁ በተደጋጋሚ ለወረዳው አስተዳደር ቢያሳውቁም ተቀባይነት ሳያገኙ መቅረታቸውን ጠቁመዋል፡፡

በአሙሩ ወረዳ የታሰሩ ከመቶ በላይ ሰዎች ባለፉት ሰባት ወራት ፍርድ ቤት አልቀረቡም

“ለፍርድ ቢቀርቡ አንድ መፍተሄ ያገኛሉ ብለን ነበር እስካሁን አልቀረቡም፡፡አንድ 8ኛ ክፍል ተማሪ እህታችን በዚሁ ምክንያት ትምህርቷን አቋርጣለች፡፡ በተሰባችንን ጨምሮ ከእኛ ሰፈር ከ17 በላይ ሰዎች በቀርቡ ታስረዋል፡፡ በአንድ ሰው ወንጅል ሌላ ሰው እንዴት ይጠየቃል በህግ ከ18 ዓመት ለሆነው ሰው ቤተሰብ ኃላፈነት እንዴት ይጠየቃል ብዬ ለመጠየቅ ሞክረአለሁ፡፡ እነሱ ግን በተሰብ ግዴታው ነው በማለት እናትና አባቴን ሲያስፈራሩ ነበር” ብሏል፡፡

ከኦሮሚያ ክልል ጋር እርቅ ያወረደው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አንድ አንጃ አባል እና የመከላከያ ሠራዊት ወታደራዊ መኮንን ጎን ለጎን ተቀምጠው
የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አንድ አንጃ በቅርቡ ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት ጋር እርቅ አውርዷልምስል Oromia communication

ጫካ የገቡ ልጆቻቸውን እንዲያመጡ ቤተሰባቸው ታስረዋል

በዚሁ ጉዳይ ላይ ምላሽ የጠየቅናቸው የአሙሩ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ዲንሳ ዱጉማ በወረዳው ልጆቻቸው ከታጣቂዎች ጋር የተቀላቀሉ የቤተሰብ አባላትን ማሰራቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ታስረዋል የተባሉትን ሰዎች ብዛት 130 አይደርስም ያሉ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በጣቢያቸው ታስሮ የሚገኙትን የሰው ብዛት ለመናገር ግን አልፈለጉም። ሆኖም 30 የሚደርሱ ሰዎች ታስሮ ከነበሩት ሰዎች መካከል ከእስር መለቀቃቸው ተናግረዋል፡፡

“ቤተሰብ ልጆቹን ከቻለ እንዲያመጣ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ቤተሰብ መያዙ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን 130 የተባለው ውሼት ነው፡፡ በየጊዜው እየጠየቅን፣እያጣራን ልጆቻቸውን እንዲያመጡ አንድ ወርና ሁለት ወር ይሰጣቸዋል፡፡ ታስሮም ብዙዎች እየተለቀቁ ነው፡፡”

በሆሮ ጎደሩ ወለጋ ዞን ስድስት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ

በአካባቢው ልጆቻቸው ወደ ታጣቂዎች የተቀላቀሉ የቤሰተብ አባላት ታጣቂዎቹ የት እንዳሉ እንደማያውቁ እና ከቤተብ ጋር ከተለያዩ ረጅም ጊዜ እንደሆናቸው በመግለጽ ጉዳዩን የወረዳው አስተዳደር ከታጣቂዎች ጋር መነጋገር እንጂ ወደ ቤተሰብ ማምጣት የለበትም ሲሉ ይናገራሉ፡፡ ልጆቻቸው ለሸፈቱት ቤተሰብ ለምን ተጠያቂ ይሆናል ብለን የጠየቅናቸው የአሙሩ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ዲንሳ ዱጉማም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

“በዚህ አካባቢ ያደጉና ቤተሰብ ጋር እየኖሩ መልሰው እየወጉን ነው፡፡ ከልጆች ዕድሜ ጋር ተያይዞ ከህግ አንጻር ቤተሰብ ላይጠየቅ ይችላል ነገር ግን ልጆቻቸውን እየመለሱ ያሉም አሉ፡፡ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ቢሆኑም ቤተሰብ ጋር እየኖሩ ነው። ታጥቆ ተደብቆ ግን ጥቃት ያደርሳሉ” የሚል ምላሽ ሰጥቷል። በአሙሩ ወረዳ የሚከሰቱት የጸጥታ ችግሮች የአካባቢውን ነዋሪ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ለከፋ ችግር አጋልጦ መቆየቱ በተደጋጋሚ ተዘግበዋል። 

ነጋሳ ደሳለኝ

እሸቴ በቀለ 

ታምራት ዲንሳ