በዋግ ኸምራ ህፃናት፣ አጥቢ እና ነፍሰጡር እናቶች ለሥርዓት ምግብ እጥረት ተጋልጠዋል ተባለ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 22 2017ዶይቼ ቬሌ ያነጋገራችው የዳህና፣ የፃግብጂ፣ የሳህላ ሰየምትና የአበርገሌ ወረዳዎች ነዋሪዎች ባለፈው ክረምት የነበረው ዝናብ ባስከተለው ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት ህብረተሰቡ የሚላስ የሚቀመስ በማጣት አካባቢውን እየተወ በስደት ላይ ነው ብለዋል፡፡
አስተያየታቸውን ከሰጡን ነዋሪዎች መካከል የፃግብጂና የአበርገሌ ወረዳዎች ነዋሪዎች እንዳሉት፣ በችግሩ ምክያት ሰዎች ስደት ጀምረዋል፡፡
“የምግብ እጥረት የሚባለው በጥቅሉ በወረዳው አለ፣ ሠዎች እየተራቡ ነው። ወደ ስደት እየተጓዙ ጭምር ነው፣ ቤቴ መንገድ ዳር ነው በየቀኑ እናቶች ልጅ አዝለውና አቀፈው ስደት ሲሄዱ እያየሁ ነው፡፡” ሲሉ የፃግብጂው አስተያየት ሰጪ ያስረዱት፡፡
የአበገሌ ወረዳ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው ሠዎች ከተልያዩ አቅጣጫዎች ወደ አበርገሌና ትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች እየተሰደዱ እንደሆነ ማየታቸውን አብራርተዋል፡፡
የሳህላ ሰየምትና የዳህና ወረዳዎች አስተያየት ስጪዎች በበኩላቸው፣ በፀጥታ ችግሩ ምክንያት መንግዶች እንደልብ ማስኬድ ባለመቻላቸው ተንቀሳቀሶ ለመስራትና ለመሰደድም እደሉን አላገኘንም ነው ያሉት፡፡
“በፀጥታ ችግር ተንቀሳቀሶ መስራት አለተቻልም” የሳህላ ሰየምት ወረዳ ነዋሪ
የሳህላ ሰየምት ነዋሪ እንደሆኑ የነገሩን አንዲት እናት እንዳሉት በፀጥታ ምክንያት መንግዶች አያንቀሳቅሱም፣ የቀን ሥራ ተንቀሳቅሶ ለመስራትም አስቸጋሪ እንደሆን ገልጠዋል፣ ህብረተስቡ ለከፍተኛ ረህብ ተጋልጧል ብለዋል፣ የአካባቢው ነዋሪ “ቀን ጨልሞበታል” ሲሉ ነው የችግሩን አሳሳቢነት ያስረዱት፡፡
የዳህና ወረዳ አስተያይት ስጪ “ከረሀቡ ባለፈ ህፃናቱን የሚያሳክክ በሽታም ተከስቷል፡፡” ነው ያሉት።
የጋዝጊብላ ወረዳ ዋና አስትዳዳሪ አቶ አበባው ደሳልኝ 900 ህፃናት ለከፍተኛ የምግብ እጥረት የተጋለጡ ቢሆንም እርዳታ ያገኙት ከ400 እንደማይበልጡ አስረድተዋል፣ የምግብ እጥርቱ በከፍተኛ ሁኔታ በመኖሩን አጠቢ እናቶችና ነፍሰ ጡሮች እጅግ እየተጎዱ ነው ብለዋል። የአቅርቦት እጥረት በመኖሩ ህዝቡ በከፍተኛ ችግር ላይ ነው መሆኑን ገልጠዋል፣ ከፍተኛ የትራንስፖርትና የፀጥታ ችግር በመኖሩ ተርጂዎች የ 7ና 8 ሰዓት መንገድ በመሄድ የምትገኝ እርዳታን ለመቀበልም ችግሩ ቀላል እንዳልሆን ነው ያብራሩት።
የሰሜንና ምዕራብ አማራ ክልል ተዘግተዉ የነበሩ ት/ቤቶች ተከፈቱ
የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት መከተል ኃላፊ ሲስተር ክበር ሞገስ በበኩላቸው በከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥርዓተ ምግብ እጥረት ያለባቸው 193 ህፃናት ተለይተው በጤና ተቋማት ህክምና እየተደረገላቸው እንደሆን ገልጠዋል፣ ከ1ሺህ 900 በላይ በመካክልኛ የሥርዓተ ምግብ እጥረት ውስጥ ያሉ ህፃናትና ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ውስጥ ያሉ 1 ሺህ 400 አጠቢና ነፍሰጡር እናቶች እርዳታ እያገኙ አይደለም ብለዋል።
በዋግኽምራ ከግማሽ በላይ አጠቢና ነፍሰ ጡር እናቶች የሥርዐተ ምግብ እጥረት አለባቸው
የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አሰፋ ነጋሽ የተመጣጠን ምግብ እጥረቱ በተለይ በነፈስጡርና አጥቢ እናቶችና ህፃናት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረስ እንደሆን ነው ለዶይቼ ቬሌ የተናገሩት፡፡ ችግር ላይ ያሉ ህፃናትንና እናቶችን ቁጥር በአህዝ ለመናገር ፈቃደኛ ባይሆኑም 57% እናቶችና 36% ህፃናት በከፍተኛ የአልሚ ምግብ እጥረት ላይ ናቸው ብለዋል።
የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አደጋ መከላከልና ምግብ ዋሰትና መምሪያ ኃላፊ አቶ ምህረት መለአኩ በብሔረሰብ አስተዳደሩ የተከሰተው ድርቅና ለችግር የተጋልጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በጥናት መለየታቸውን አመልክተዋል፡፡ እርዳታ በቅርቡ እንደሚሰራጭም ገልጠዋል።
በብሔረስብ አስተዳድሩ 242 ሺህ ወግኖች የእለት ምግብ ፈላጊዎች ናቸው
እንደኃላፊው በብሔረስብ አስተዳደሩ በተደርጉ ጥናቶች መስረት 49 ሺህ 165 ሔክታር መሬት ባለፈው ክረምት ጉዳት ደርሶበታል፣ በተልይ ጉዳቱ በዳህናና ጋዝጊብላ ወረዳዎች መሬቱ በመጎዳቱ በቀጣይ ዓመት ምርት እንደማይሰጥ በጥናቱ ታውቋል ብለዋል። 2 ሚሊዮን 400 ሺህ ኩንታል ምርት ተጠብቆ የነበር ቢሆንም ግማሽ ሚሊዮን ኩንታል ምርት በነበረው የክረምት ከባድ ዝናብ፣ ጎርፍና ናዳ ወድሟል ነው ያሉት። ብዚህም ምክን ያት 242 ሺህ ወገኖች ለምግብ እህል እጥረት መጋለጣቸውን አመልክተዋል።
በዋግኸምራ አበርገሌ ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ህፃናት እየሞቱ ነው
የአማራ ክልል አድጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋው ባታብል ብሔረስብ አስተዳደሩ ያስጠናው ጥናት ከፀደቀ በኋላ ከጥር/2017 የመጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ እርዳታ ወደ ቦታው ይጓጓዛል ብለዋል።
በክልሉ ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በተከሰተ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በወረዳው ያሉ ህፃናት በከፍተኛ ችግር ላይ እንደሆኑ ባለፈው ሳምንት በተለያዩ መገናኛ ብዙሐን መዘገቡ ይታወሳል። በአማራ ክልል በተፈጥሮና በሠው ሰራሽ በተከሰቱ አደጋዎች ምክንያት ወደ 1 ሚሊዮን 500 ሺህ ሠዎች የእለት ምግብ እርዳታ ፈላጊዎች ናቸው።
ዓለምነው መኮንን
እሸቴ በቀለ
ታምራት ዲንሳ