1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የነዳጅ ዋጋ ንረትና ሥዉር ገበያ በአሽከርካሪዎች ላይ ያደረሰዉ ችግር

ረቡዕ፣ ጥር 7 2017

ሌላው አስተያየት ሰጪ ተሽከርካሪውን ከባንክ ብድር ወስዶ መግዛቱን ጠቅሶ በቤንዚን እጥረቱ ምክንያት ሰርቶ ብድር መመለስ እንዳልቻለ ገልጧል፣ አንዴ ነዳጅ ከቀዳ ሌላ ጊዜ ለመቅዳት ሳምንት እንደሚጥብቅ አመልክቷል፣ ያን ላለማድረግ ደግሞ በውድ ዋጋ ከህገወጥ ነጋዲዎች ቤንዚን ገዝቶ እንደሚሰራ ነው ያስረዳው።

https://p.dw.com/p/4pALs
ባሕርዳር የሚኖሩና የሚሠሩ አሽከርካሪዎቹ እንደሚሉት ቤንዚን ለማግኘት ለተከታታይ ቀናት ሰልፍ ለመያዝ ይገደዳሉ።ወረፋ ለማግኘት በቀን አንድ መቶ ብር ለመክፍል ይገደዳሉ
ባሕርዳር የባልሶስት እግር ታክሲና በተለምዶ የዳማት አነስተኛ ተሽከርካሪ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች በየጊዜው በሚጭምረው የቤንዚን ዋጋ፣ ቤንዚን ለማግኘት በሚደረግ አሰልቺ ሰልፍና በህገወጥ የቤንዚን ዝውውር ተማርረዋልምስል Alemenew Mekonnen/DW

የነዳጅ ዋጋ ንረትና ሥዉር ገበያ በአሽከርካሪዎች ላይ ያደረሰዉ ችግር

            

ከጊዜ ወደጊዜ የሚያሻቅበው የቤንዚን ዋጋና ህገወጥ የነዳጅ ሽያጭ ሥራቸውን እንዳጎለባቸዉ የአማራ ክልል የህዝብ አገልግሎት ስጪ ተሽከርካሪ  ባለንብረቶች አስታወቁ።የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በበኩሉ ህገወጥነትን ለመከላከል እየሰራ እንደሆን አመልክቷል።ቢሮዉ  ባልፉት 6 ወራት ብቻ 250ሺህ ሊትር ነዳጅ ዘይት በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር መያዙንም ቢሮዉ ገልጧል።አለምነዉ መኮንን ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

በተለያዩ የባሕር ዳር ከተማ ማደያዎች ነዳጅ ለመቅዳት ሰልፍ ይዘው ያገኘናችውና ለዶይቼ ቬሌ አስተያየታቸውን የሰጡ የባልሶስት እግር ታክሲና በተለምዶ የዳማት አነስተኛ ተሽከርካሪ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች በየጊዜው በሚጭምረው የቤንዚን ዋጋ፣ ቤንዚን ለማግኘት በሚደረግ አሰልቺ ሰልፍና በህገወጥ የቤንዚን ዝውውር ተማርረዋል።

ነዳጅ ከማደያ ለመቅዳት ፈተናው ብዙ ነውተጠቃሚዎች

አስተያየታቸውን ከሰጡን ወጣቶች መካክል አንዱ “ቤንዚን ለመቅዳት ቀናት ማስቆጠሩን አመልክቶ አማራጭ በማጣት እንጂ ሥራውን የመስራት ፍላጎት የለኝም” ብሏል።

“ቤት ከመቀመጥ ወጥቶ መዋሉ ይሻላል ከሚል እንጂ ሥራው ትርፍ የለውም ነው” ያለው።

ሌላው አስተያየት ሰጪ ተሽከርካሪውን ከባንክ ብድር ወስዶ መግዛቱን ጠቅሶ በቤንዚን እጥረቱ ምክንያት ሰርቶ ብድር መመለስ እንዳልቻለ ገልጧል፣ አንዴ ነዳጅ ከቀዳ ሌላ ጊዜ ለመቅዳት ሳምንት እንደሚጥብቅ አመልክቷል፣ ያን ላለማድረግ ደግሞ በውድ ዋጋ ከህገወጥ ነጋዲዎች ቤንዚን ገዝቶ እንደሚሰራ ነው ያስረዳው። መንግሥት በነዳጅ ላይ ዋጋ ቢጭምርም በትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማስተካከያ ባለማድረጉ ለኪሳራ እየተዳረጉ እንደሆነም አክሏል።

ቤት ላለመዋል እንጂ ሥራው አዋጪ አልሆን ብሏልየባጃጅ አሽከርካሪ

ሥራ ላልማቆም ሰሞኑን በተደረገው ጭማሪ መሰረት ከማድያ በ102 ብር መግዛት የሚቻለውን አንድ ሊትር ቤንዚን እስክ 300 ብር ከህገወጥ ነጋዴዎች ለመግዛት እንደተገደደ ዛሬ በባሕርዳር ከተማ አንድ ነዳጅ ማደያ ቤንዚን ለመቅዳት ሰልፍ ይዞ ያገኘንው ወጣት ነግሮናል።

ባልፉት 6 ወራት ብቻ 250ሺህ ሊትር ነዳጅ ዘይት በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር መያዙን የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ገልጧል
የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በበኩሉ ህገወጥነትን ለመከላከል እየሰራ እንደሆን አስታዉቋል።ምስል Alemenew Mekonnen/DW

ሰልፍ ለምያዝ በቀን 100 ብር ለጥበቃ እንድሚክፍል የገለጠልን ሌላው ወጣት፣ “4 እና 5 ቀናት በምንቆምበት ወቅት እስከ 500 በር እንከፍላልን” ሲል አመልክቷል፣ በዚህ ሁኔት ሰርቶ ቤተስብ ለማስተዳደር እንደተቸገረ ገልጧል።

በህገወጥ ሲዘዋወር የነበር 250 ሺህ ሊትር ነዳጅ በቁጥጥር ስር ውሏልየአማራ ክልል ንግድና ገብያ ልማት ቢሮ

የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኢብራሒም ሙሐመድ ባልፉት 6 ወራት ሀገወጥነትን ለመከላከል ሰፊ ሥራ መሰራቱን ጠቁመው በዚህም በህገወጥ መንግድ ሲዘዋወር የነበር 250 ሺህ ሊትር ነዳጅ በቁጥጥር ስር ውሎ ለመንግሥት ገቢ ሆኗል ብለዋል።

የአማራ ክልል መንግሥት በነዳጅ ግብይትየሚታየውን ህገወጥነት ለመከላከል ትኩርት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆንም ኃላፊው ተናግረዋል።

“250 ነዳጅ ቦቴዎችና 19 ማደያዎች 6 ወራት ከሥራ ታግደዋልቀጥናዊ ትስስር ሚኒስቴር

የፌደራል ንግድና ቀጠናዊ ትብብር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ትናንት አዲስ አበባ  ውስጥ በሰጡት መግለጫ በህገወጥ መንገድ ትርፍ ለማግኘት ከ10 እስከ 15 ቀናት ነዳጅ ጭነው ጥሻ ውስጥ ተደብቀው የነበሩ 250 የነዳጅ ቦቴዎች በቁጥጥር ስር ውለው ቅጣት ተጥሎባቸዋል ብለዋል። 100 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ቅጣት የተጣለባቸው ሲሆን ለቅጣይ 6 ወራትም የነዳጅ ምርት እንዳያዘዋውሩ መታገዳቸው ተገልጧል፣ “ተባባሪ ነበሩ” የተባሉ 19 ማደያዎችም ለ6 ወራት ከግብይት መታገዳቸው በመግለጫው ተመልክቷል።

የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በበኩሉ ህገወጥነትን ለመከላከል እየሰራ እንደሆነ  አመልክቷል።በየጊዜዉ ለሚያሻቅበዉ የቤንዚን ዋጋ ግን ሁነኛ መልስ የለዉም
ባሕርዳር ከተማ ዉስጥ አገልግሎት የሚሰጡ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎችና ሌሎች ታክሲዎች በየጊዜዉ የሚጨምረዉ የቢንዚን ዋጋና የሥር ወገበያ ሥራቸዉን እያጎለዉ መሆኑን አስታዉቀዋል።ምስል Alemenew Mekonnen/DW

ዓለምነው መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ