የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ስለ ኢሬቻ በዓል ዝግጅት ምን ይላሉ?
ዓርብ፣ መስከረም 25 2016ማስታወቂያ
በነገው እለት በአዲስ አበባ ለአምስተኛ ተከታታይ ጊዜ የሚከበረውን የኢሬቻ ሆራ-ፊንፊኔ ክብረ በዓል ለማክበር እንግዶች በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ መዲናዋ እየተመሙ ነው።
አዲስ አበባ ውስጥ ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ለጸጥታ ጥበቃው ሲባል በተለይም በዓሉ ወደ ሚከበርበት መስቀል አደባባይ እና ስታዲየም የሚወስዱ በርካታ መንገዶች ተዘግተዋል።
የ2015 ዓ.ም. የኢሬቻ ሆራ ሀርሰዲ በቢሾፍቱ ዛሬ ተከበረ
በዚህ በዓል መዳረሻ ከመንገዶች መዘጋጋት ጋር ተያይዞ የእለት ህይወቱ በእግር ረዘም ያሉ መንገዶችን ከመጓዝ ጀምሮ በተለያዩ መንገዶች የሚፈተኑ እንዳሉ ተጠባቂ ነው፡፡ በዓሉ በሰላም ተከብሮ ይጠናቀቅ ሆን በሚል ስጋት ውስጥ የሚገቡ የማህበረሰብ አካላትም አይታጡም።
የበዓሉ ታዳሚዎች በስፋት ወደ ከተማዋ ከመግባታቸው አንጻር እድሉን ወደ ንግድ ቀይረው ለመጠቀም በዓሉን በጉጉት የሚጠብቁም በርካቶች ናቸው። ሥዩም ጌቱ በመዲናዋ ጎዳና ላይ ዞር ዞር ብሎ ከነዋሪዎች አስተያየት አሰባስቧል፡፡ ከሕዝብ የተሰበሰቡትን አስተያየቶች ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ
ሥዩም ጌቱ
እሸቴ በቀለ
ሸዋዬ ለገሠ