1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦፓል ማዕድን አውጪ ወጣቶች ስሞታ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 25 2017

አስተያየታቸው ለዶቼ ቬለ የሰጡ ማእድን ቆፋሪዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ቆፍረን ያወጣነዉን የኦፓል ማእድን አስርና ሀያ ሽህ የሚሸጥ ቢሆንም ባለ ቤትነን በሚሉ ሰዎች በሁለት ሽህ ብር አልያም በነፃ ይወሰድብናል ይላሉ።

https://p.dw.com/p/4onVm
Äthiopien Opal-Grube
ምስል South Wollo Zone Communication

የኦፓል መዓድን አውጪ ወጣቶች ስሞታ

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ቆቅ ዉሀ በተባለ ስፍራ የኦፓል  ማእድን በማዉጣት ላይ የነበሩ ወጣቶች በሠዉ ሰራሽ ዋሻ ዉስጭ በተፈጠረ ናዳ ምክንያት በዚያዉ ተቀብረዉ  እስከ አሁን ሳይገኙ 11 ወራቶች ቢቆጠሩም በወረዳዉ የተለያየ ስፍራ የሚገኙ ወጣቶች የኦፓል ማዕድንን አስቸጋሪ በሚባል ሁኔታ  በማዉጣት ስራ ተሰማርተዋል ይገኛሉ።

በወረዳዉ 30 ማህበራት  ኦፓልን በህጋዊ መንገድ  የማዉጣት ፈቃድ ቢኖራቸዉም  በርካቶች ግን የገቢምንጫቸዉ አድርገዉ ይህንን አስቸጋሪ ስራ በግል ይከዉናሉ በወረዳዉ በግል የኦፓል ማእድን በማዉጣት የተሰማሩ ወጣቶችም የማእድን ስፍራዉ የኛ ነዉ በሚሉ ሰዎች የጉልበት ብዝበዛ እየተከወነብን ነዉ ሲሉ ይናገራሉ።

አስተያየታቸው ለዶቼ ቬለ የሰጡ ማእድን ቆፋሪዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ቆፍረን ያወጣነዉን የኦፓል ማእድን አስርና ሀያ ሽህ የሚሸጥ ቢሆንም ባለ ቤትነን በሚሉ ሰዎች በሁለት ሽህ ብር አልያም በነፃ ይወሰድብናል ይላሉ።

አሁን ላይ በወረዳዉ የተለያዮ ቀበሌዎች የሚከወን የኦፓል ማእድን ማዉጣት ስራ በህገወጦን የሚመራ ነዉ የሚሉት ማእድን ቆፋሪዎቹ  መንግስት ተገቢዉን ጥቅም እያገኘ አይደለም በማለት አስተያየታቸውን አክለዋል።

በአማራ ክልል በመንግስትና በፋኖ ታጣቂ ሀይሎች መካከል እየተደረገ የሚገኘዉ ጦርነት የኦፓል ማእድን ለማዉጣት አስቸጋሪ ከማድረጉም በዘለለ ለእንግልት ተዳርገናል በማለት ወጣቶቹ ያማርራሉ።
የደላንታ ወረዳ ማእድን ጽህፈት ቤት የማእድን ስራዎች ፈቃድ መስጠትና ማስተዳደር ቡድን መሪ የሆኑት አቶ በሪሁን አበባዉ በበኩላቸዉ አሁን ላይ 20 ወጣቶችን ህይዎት ከቀጠፈዉ የቆቅ ዉሀ 018 ቀበሌ የማእድን ስፍራ በስተቀር ሌሎቹ ኦፓል እየወጣባቸዉ ቢሆንም ባለዉ የፀጥታ ችግር ምክንያት ምንም አይነት መረጃ ለመስጠት እንቸገራለን ሲሉ ተናግሯል።

በየአመቱ ከ30 ሺህ ኪሎ ግራም የኦፓል ማእድን ለማዕከላዊ ገበያ ሲያቀርብ የነበረዉ የደላንታ ወረዳ አሁን በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል እየተካሄደ በሚገኘዉ ጦርነት መገኘት የሚገባዉ ሀብት እየተገኘ አይደለምም ብለዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን ማእድን መምሪያ ኃላፊ አቶ አህመድ አበባዉ በበኩላቸዉ በባህላዊ መንገድ እየተከወነ የሚገኘዉን የኦፓል ማእድን የመቆፈር ተግባር ለማዘመን አቅም የለንም ይላሉ።
ኢሳያስ ገላው
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
ታምራት ዲንሳ